“በሌሎች የድርጅቱ ምርቶች ላይ የማጣራት ስራ እየተሰራ ነው”

Date:

የኢትዮጵያ የመድሃኒትና የምግብ ቁጥጥር ባለስልጣን “Nestle” ከሚያመርታቸው የጨቅላ ህፃናትና የታዳጊ ህፃናት የምግብ ምርቶች፦

➡ የምርት መለያ NAN special pro HA 0-12፣
➡ የባች ቁጥሩ 51660742F3 ፣
➡ የተመረተበት ቀን 15 June 2025 ፣
➡ የሚያበቃበት ቀን 15 December 2026 እና 800 ግራም ክብደት ምርት ላይ ብክለት ማጋጠሙንና ጥቅም ላይ እንዳይውሉና እንዲሰበሰብ የጥንቃቄ መልዕክት መላኩን ገልጿል።

ምርቱ በባለስልጣኑ ፈቃድ ያልተሰጠውና ጥቅም ላይ እንዲውል ያልተፈቀደለት መሆኑን ያስታወቀው ባለስልጣኑ ምርቱ በተለያዩ መንገዶች ገበያ ላይ ሊኖር የሚችልበት ሁኔታ እንዳለ ጠቅሶ ለህብረተሰቡ ማቅረብ የተከለከለ መሆኑና ህብረተሰቡ እንዳይገዛና ጥቅም ላይ እንዳያውል አሳስቧል።

ባለስልጣኑ ምርቱን ያገኘ ወይም የያዘ አካል ለይቶ በማስቀመጥ ለባለስልጣኑ እንዲያሳውቅ ጥሪ አቅርቧል።

በሌሎች የድርጅቱ ምርቶች ላይ የማጣራት ስራ እየተሰራ እንደሚገኝና ተጨማሪ መረጃ እንደሚያቀርብ ገልጿል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ10 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ ጥቅምት 12 ቀን 2019...

ዳሸን ባንክ እና ሼባ ማይልስ የፕላቲንየም ብራንድ የማስተር ካርድ ይፋ አደረጉ

ዳሸን ባንክ እና ሼባ ማይልስ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ደንበኞች የፕሪሚየም...

የአሜሪካ የደህንነት ኃላፊ ኢራንን አስጠነቀቁ

ቡሔራዊ ደህንነት ዳይሬክተር ጄይ ክላይተን አርብ ዕለት ኢራን በውጭ...

ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ  በአመት ከ1.1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ታጣለች

85 በመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ በግብርናው ዘርፍ የተሰማራ ሲሆን...