በሰው ሰራሽ አስተውህሎት የሚደረጉ የሃቅ ማጣራቶችን ማመን እንችላለን?

Date:

የሰው ሰራሽ አስተውህሎት ቻትቦቶችን (AI chatbot) ሃቆችን ለማጣራት መጠቀም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል። እነዚህ ቻትቦቶች የሚሰጡት ምላሽ ግን ሁሌም ልናምነው የሚገባ አይደለም።

በቅርቡ ቴክራዳር በተሰኘ ተቋም የተደረገ ጥናት 27 በመቶ አሜሪካውያን የተለመዱትን እንደ ጎግል ያሉ የመፈለጊያ መንገዶች ከመጠቀም ይልቅ የሰው ሰራሽ አስተውህሎት መተግበሪያዎችን ሲጠቀሙ እነዚህ መተግበሪያዎች የሚሰጡትን መረጃ ምን ያህል ትክክል ነው የሚለው ግን ጥያቄ ነው።

ቢቢሲ ባደረገው ጥናት በራሱ በቢቢሲ የተሰሩ ዜናዎችን መሰረት አድርጎ እንደ ‘CHATGPT, COPILOT,GEMINI እና PERPLEXITY’ ያሉ የሰው ሰራሽ አስተውህሎት መተግበሪያዎችን ጥያቄ ሲጠይቅ 13 በመቶዎቹ በዜናዎቹ ውስጥ የተጠቀሱትን ቀይረዋል አሊያም ደግሞ ያልተጠቀሰ ነገር አካተዋል።

የሰው ሰራሽ መተግበሪያዎቹ የተሳሳተ መረጃና ምንጭ ከማቅረባቸው በተጨማሪ  በአግባቡ መመለስ የማይችሉትን ጥያቄ ሲጠየቁ እየፈጠሩ እያቀረቡ ነው።

የሰው ሰራሽ አስተውህሎት የሚሰጠንን መረጃ ከተለያየ ምንጮች የሚያሰባስብ ሲሆን መጀመሪያውንም ምንጮቹ የተዛቡና የተሳሳተ ከሆኑ መተግበሪያዎቹ ተገቢውን ምላሽ ሊሰጡን አይችሉም የሚለው ሃሳብ ለችግሩ በምክንያትነት ከሚቀርቡት ዋነኛው ነው።

በተጨማሪ እንደ Grok ያሉ የሰው ሰራሽ አስተውህሎት መተግበሪያዎች በፖለቲካ ከመቃኘታቸው አንፃር የተዛባ መረጃን ይሰጣሉ።

እንደዚሁም መተግበሪያዎቹ በሰው ሰራሽ አስተውህሎት የተሰሩ ምስሎችን እንደ እውነተኛ ምስሎች እየሰየሙ ነው።

ባለሙያዎች ቀለል ያሉ የሃቅ ማጣራቶችን በሰው ሰራሽ አስተውህሎት መተግበሪያ ማከናወን እንደሚቻል ቢመክሩም ሙሉ ለሙሉ እነሱ ላይ ጥገኛ መሆንን ግን አያበረታቱም።

DW Amharic

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...

“እኔ እስካለሁ ድረስ ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት አትሆንም!”

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት ሰኔ 5 ቀን...

አገር እንዲህ ዓይንህን ለአፈር ይባላል?

በተጀመረው የአለም ዋንጫ ደቡብ አፍሪካ በሜክሲኮ መሸነፏን ተከትሎ አፍሪካ...

አሜሪካ እና ኢራን የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት በ24 ሰዓት ውስጥ እንደሚፈራረሙ ፓኪስታን አስታወቀች

ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን በሰላም ድርድሩ ማዕቀፎች ላይ መስማማታቸውን...