በቤተክርስቲያን ሥርዓተ እምነት ላይ የወንጀል ድርጊት በመፈጸም የተጠረጠሩት  በሕግ ቁጥጥር ሥር ውለዋል

Date:

ራሳቸውን ‹‹መሪጌታ›› ጽጌ ስጦታው እና ‹‹መሪጌታ›› ምስጢረ መዝገቡ ብለው የሚጠሩ ግለሰቦች በቅድስት ቤተክርስቲያኛችን ሥርዓተ እምነት ላይ በወንጀል የሚያስጠይቅ ድርጊት ፈጽመዋል  በሚል  ተጠርጥረው የወንጀል አቤቱታ በቀረበባቸው መሠረት የፌደራል ወንጀል ምርመራ ቢሮ በዛሬው ቀን ተጠርጣሪዎችን በሕግ ቁጥጥር ሥር በማዋል የወንጀል ምርመራውን በማጣራት ላይ እንደሚገኝ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን የሕግ ባለሙያዎች ዐቢይ ኮሚቴ አባል ጠበቃ አያሌው ቢታኔ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

ጠበቃ አያሌው አያይዘው እንደገለጹት ከግለሰቦቹ በተጨማሪ  እንዳልካቸው ዘነበ  የተባለ ግለሰብ  በተመሳሳይ ከዚህ ቀደም በቤተክርስቲያናችን ላይ  ፈጽሞታል ተብሎ በተጠረጠረበት ስም ማጥፋት በቅርቡ  በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውሎ  ቃሉን  ሰጥቶ   በዋስትና መለቀቁን እና በዐቃቤ ሕግ በኩልም የወንጀል አቤቱታ ክስ ቀርቦ በሒደት ላይ  እንደሚገኝ አያይዘው ገልጸዋል። 

የሕግ ባለሙያዎች ዐቢይ ኮሚቴ አባል ጠበቃ አያሌው ቢታኔ በሰጡት መረጃ  ኮሚቴው  ወደ ፊት ጉዳዩን ተከታትሎ የሚያሳውቅ መሆኑን ገልጸዋል።

©EOTC TV

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የተላለፈ ጥሪ

በክልላችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያደገ የመጣው የተሳሳተ ስሌት የወለደው...

በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ በከባድ መሳሪያዎች የታገዘ  የተኩስ ልውውጥ ተካሄደ

ለዓለም የንግድ ሰንሰለት እጅግ ስትራቴጂካዊ በሆነው የሆርሙዝ ባህረ ወሽመጥ...

የሲ.ኤን.ኤን መስራች ቴድ ተርነር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የዓለማችን ግዙፍ የዜና አውታር ሲኤንኤን መስራች ቴድ ተርነር በ87...

የኢትዮጵያ አጠቃላይ ብድር 51.8 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ይፋ ሆኗል

ኢትዮጵያ  በድጋፍ መልክ ከአሜሪካ በየዓመቱ  በመንግስት በኩል ፈሰስ የሚደረግ...