በቻይና የፍቅረኛው እጅ በአፉ ውስጥ ገብቶ አልወጣ ያለው ግለሰብ

Date:

በቻይና ጂሊን ግዛት ውስጥ በሚገኝ ሆስፒታል ያሉ ዶክተሮች አስገራሚ የሆነ ክስተት አጋጥሟቸዋል። አንዲት ሴት አስቂኝ ቪዲዮ ለመቅረጽ ስትሞክር እጇን ወደ ወንድ ጓደኛዋ አፍ ውስጥ ትከታለች።በጂሊን ግዛት ውስጥ ወደሚገኝ ሆስፒታል ድንገተኛ ክፍል ሲገቡ የሚታዩት ጥንዶች ፎቶዎች በቻይና ማህበራዊ ሚዲያ ላይ በስፋት ታይተዋል።ግለሰቧ ወደ ፍቅረኛዋ አፍ ውስጥ እጇን ካስገባች በኃላ ለማውጣት ስትሞክር የአፉ ጡንቻ ይደነድን እና እጁ ይጣበቃል።

ወጣቷ ከአፉ ላይ እጇን ለማውጣት ደጋግማ ብትሞክርም ባለመቻሏ የሕክምና እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ትወስናለች።ዶክተሮች ታሪካቸውን እስኪሰሙ ድረስ በጥንዶቹ ግራ ተጋብተው እንደነበር ተሰምቷል። የወንድ ጓደኛዋ ፊት ቀስ በቀስ ወደ እየቀላ እጇን ከአፉ ነፃ ለማውጣት የምታደርገው ጥረት ሁሉ ከንቱ እንደሆነ ተናግራለች። አፉን መዝጋት ባለመቻሉ እና ከጉሮሮው ያለማቋረጥ አስጨናቂ ድምፅ መውጣት ጀመረ። ይባስ ብሎ በጡንቻው መኮማተር ምክንያት ጥርሶቹ እጆቿ ላይ ተጣበቁ።  “ምራቁ እስከ ክርኔ ድረስ ይመጣ ነበር” ስትል ተናግራለች። “እጄ በስጋ መፍጫ ውስጥ የተጣበቀ ያህል ተሰማኝ” ስትል አክላለች።

ጉዳዩን የተከታተሉት ዶክተር ዣንግ ሚንዩአን እንዳሉት የልጅቷ እጅ ተጣብቆ የቀረው የወንድ ጓደኛዋ የመንጋጋ ጡንቻ በመያዙ አፉን እንይከፍት አድርጎታል።ችግሩን ለመቅረፍ የሆስፒታሉ ሰራተኞች ልዩ አፍ መክፈቻ መሳሪያ ተጠቅመው መንጋጋውን በማስፋት በተወሰነ ቦታ ላይ ጡንቻን የሚያስታግስ መርፌ ተጠቅመዋል። ከ20 ደቂቃ በኋላ የወጣቷ እጅ እንዲወጣ ተደርጓል። አንድ ሰው መንጋጋውን እንዲከፈት ማስገደድ የነርቭ ጉዳት ወይም የመንገጭላ መበታተን ሊያስከትል እንደሚችል ባለሙያዎች አስጠንቅቀዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት በዛሬ ዕትሟ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ ነሔሴ 16 2018 ዓ.ም ገበያ...

ቱርክ ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ የእስር ማዘዣ አወጣች

ቱርክ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ ዓለም አቀፍ...

በመቀለ የሚካሄደው የአሸንዳ በዓል የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ተሰረዘ

በትግራይ በርካታ ታዳሚ በሚገኝበት በየዓመቱ የሚከበረው የአሸንዳ ባህላዊ በዓል...

የኢትዮጵያ ፖስታ 3 ሺሕ የሚጠጉ ቅርንጫፎቹን ወደ ባንክ ኤጀንትነት ለመቀየር እንቅስቃሴ ጀመረ

የኢትዮጵያ ፖስታ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ 3 ሺሕ በሚጠጉ ቅርንጫፎቹ...