በ500 ብር የቤት ኪራይ ክፈሉልን !!

Date:

የምወዳችሁ የፌስቡክ ጓደኞቼ !!

ፌስቡክ ላይ እንደቀልድ ህይወትን እየተካፈልን፣ እያየንም እያሳየንም 15 ዓመት ኖርን አይደል? …በዚህ ሁሉ ዘመን ለመጀመሪያ ጊዜ “ተባበሩኝ” ያልኳችሁ ደግሞ የዛሬ አመት ነበር፡፡ እነሆ በዓመቱ ይህንኑ ጥያቄ ይዤ መጥቻለሁ፡፡

እኔ ኦቲዝም ላይ አድቮኬሲ ስሰራ ትንሽ ቀደም ብልም በግፉዓን ድምጽነቱ የምናውቀው የሸገሩ ግርማ ፍስሃ “አግዝሃለሁ!” ብሎ ከጎኔ ቆሟል፡፡ አሁን ሁለታችንም የነህምያ ኦቲዝም ማዕከል የበጎ ፍቃድ አምባሳደሮች ነን፡፡

( ‘ሹመት ያዳብር’ ብላችሁ ጉድ እንዳታደርጉን 😄)

ነህምያ በኦቲዝም ጥላ ስር ያሉ ልጆችን ከጥገኝነት ተላቀቀው ለመደበኛ ትምህርት እንዲበቁ ሲንከባከብና ሲያሰለጥን 14 ዓመታትን አሰቆጥሯል፡፡ በግለሰብ ግቢ ኪራይ 80 የኦቲዝም ህጻናትን ይዞ ፣ ሁለት ሺህ ህጻናትን በተጠባባቂ ሊስት መዝግቦ “ደግፉኝና ልጆቼን ላስተምር ፣ ተጠባባቂዎቼንም ልድረስላቸው ” እያለን ነው፡፡

ነህምያ የቤት ኪራዩን የሚሸፍነው በአመት አንዴ ዓለምአቀፉን የኦቲዝም ወር ጠብቆ በሚያዘጋጀው ኹነት ላይ ከሚሸጠው ቲሸርት በሚያገኘው ገቢ ነው፡፡

እኔና ግርማም ቲሸርቱን ለመሸጥ ተሰማርተናል፡፡ የተለመደ ቀና ትብብራችሁን ልንጠይቅ ነው፡፡ አንድ ቲሸርት በ500 ብር ብቻ በመግዛት የነህምያን የቤት ኪራይ ወጪ ተጋሩ፡፡ መጋቢት 28 በጎልፍ ክለብ ከ EDF ጋር ባዘጋጀነው የማስ ዳንስ ትርዒትና የግንዛቤ ማስጨበጫ ኹነት ላይ በመገኘትም “ከጎናችሁ ነን!” በሉን፡፡ጊዜው የጾምና ጸሎት አይደል? መስጠታችሁ የበረከት እንዲሆንላችሁ እንለምናለን፡፡

500 ብሩን በነህምያ ኦቲዝም ማዕከል ሂሳብ ቁጥር 1000009335308 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በማስገባት ስክሪንሹት በውስጥ መስመር ላኩልኝ፡፡

ቲሸርቱን ስልኬ ላይ በ0911403884 ደውሉልኝ፣ አቀብላችኋለሁ፡፡ፖስቱን ሼር በማድረግ ብትተባበሩኝ ደግሞ ምስጋናዬ ወደር የለውም፡፡

እግዚአብሄር ያክብራችሁ! ጠይቃችሁ አትጡ !!

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...