በአማራ ክልል ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት አብዛኛውን ሴቶች ችግር እየደረሰባቸው መሆኑ ተገለጸ

Date:

በአማራ ክልል ካለው ግጭት ጋር በተያያዘ በሚፈጸመው ጾታዊ ጥቃቶች አብዛኛውን ሴቶች ችግር እየደረሰባቸው መሆኑን የክልሉ ሴቶች ማህበራት ፌደሬሽን አስታውቋል፡፡

በክልሉ የተለያ አካባቢዎች ላይ በሚስተዋሉ ግጭቶች ሳቢያ በሴቶች ላይ የሚፈጸመው ጥቃቶች መጨመራቸውን የክልሉ ሴቶች፣ ሕፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ እንዲሁም የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት ሲገልጹ ይደመጣል።

የአማራ ክልል ሴቶች ማህበራት ፌደሬሽን የተለያዩ ችግሮች ሲፈጠሩ ቀዳሚ ተጎጂዎች ሴቶች እና ሕጻናት መሆናቸውን የገለጸ ሲሆን፤ በክልሉ ጾታዊ ጥቃት የደረሰባቸውን ሴቶች የሕክምና አገልግሎት፣ የሥነ-ልቦና እና የገንዘብ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ገልጿል።

የፌደሬሽኑ ምክትል ፕሬዝዳንት ንጽህ ሽፈራው ፌደሬሽኑ በሥሩ አጠቃላይ 7 ማህበራትን ያቀፈ መሆኑን ያነሱ ሲሆን፤ ከ1 ነጥብ 98 ሚሊዮን በላይ አባል ያላቸውን የሴት አደረጃጀቶችን በአባልነት ማቀፉን አስረድተዋል፡፡

የተቋቋመበት ዋነኛ አላማም የሴቶችን ሁለንተናዊ ደህንነት ማስጠበቅ፣ በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ዘርፍ ተጠቃሚ ማድረግ መሆኑን ገልጸዋል።

“ነገር ግን የሴቶችን ሁለንተናዊ ደህንነት ለማስጠበቅ የተረጋጋ ሰላም የተጠበቀበት ቦታ ላይ መስራት ሰላም ሊረጋገጥ ይገባል” ብለዋል።

አሁን በክልሉ ባለው ሁኔታ የመጀምሪያ ተጠቂዎች ሴቶች፣ ህጻናት፣ አረጋውያንና አካል ጉዳተኞች ናቸው ያሉ ሲሆን፤ ጉዳት እየደረሰባቸው መሆኑን ጠቁመዋል።

ስለሆነም በክልሉ ዘላቂ የሆነ ሰላም ሊያመጡ የሚችሉ ሥራዎችን ፌደሬሽኑ እየሰራ መሆኑን ገልጸው፤ በሴቶች ላይ የሚከሰቱ ችግሮችን ቀድሞ የመከላከል ሥራ እና ችግሩ ከደረሰ በኃላም ፍትህ የሚገኝበትን መንገድ መኖሩን አንስተዋል።

በተለይም ግጭት ባለበት ቦታ ላይ ጾታዊ ጥቃት የሚፈጸምባቸው ሴቶች ላይ ችግሩ የከፋ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አሐዱም እነዚህን ድጋፎች ለማድረግና መደበኛ እንቅስቃሴን ለመከወን አመቺ ሁኔታ አለ ወይ? ሲል የጠየቃቸው ሲሆን፤ በክልሉ አንጻራዊ ሰላም በመኖሩ ሥራዎችን ለመስራት አመቺ ሁኔታዎች ስለመኖሩም ገልጸዋል፡፡

የአማራ ክልል ሴቶች ሕጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በ2017 ዘጠኝ ወራት ብቻ በክልሉ ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት ከ20 ሺሕ የሚበልጡ ሴቶች ወደ ወሲብ ንግድ መግባታቸውን የገለጸ ሲሆን፤ እንዲሁም ከ9 ሺሕ በላይ ሕጻናት ጎዳና ተዳዳሪ መሆናቸውንና ከ7 ሺሕ የሚበልጡ ሰዎች ደግሞ ወደ ልመና መግባታቸውን ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

(አሐዱ ሬድዮ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የተፈናቀሉ ዜጎች በተጠለሉበት አካባቢ በቋሚነት መኖር የሚያስችላቸው 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የዳሰነች ወረዳ ከበኦሞ...

ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 11ኛውን የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በደብረ ብርሃን ከተማ አስመረቀ

ታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ...

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...