በአዲስ አበባ የመሬት ሊዝ 5ኛ ዙር ጨረታ ከፍተኛው ዋጋ በካሬ 265 ሺህ ብር ተመዘገበ

Date:

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ባካሄደው 5ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ አሸናፊዎችን ይፋ አድርጓል።

በዘጠኝ ክፍለ ከተሞች ለ427 ፕሎቶች ከመጋቢት 29 እስከ ሚያዚያ 3 ቀን 2017 ዓ.ም. በተካሄደው በዚህ ጨረታ በአንድ ካሬ ሜትር ከፍተኛው ዋጋ 265 ሺህ ብር በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ተመዝግቧል።

የጨረታ ኮሚቴ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ሀብታሙ ተስፋዬ እንደገለጹት፣ በዚህ ዙር ጨረታ ከፍተኛ ተወዳዳሪነት የታየ ሲሆን፣ በተለይም ለንግድና ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውሉ ቦታዎች ከፍተኛ ዋጋ ተሰጥቷቸዋል

ይህ ውጤት ከዚህ ቀደም ጥቅምት 8 ቀን 2017 ዓ.ም. በአስር ክፍለ ከተሞች በተካሄደው በ4ተኛዉ ዙር የሊዝ ጨረታ ከነበረው ከፍተኛ ዋጋ ጋር ሲነጻጸር አነስተኛ ነው።  በወቅቱ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አንድ ካሬ ሜትር መሬት በ306 ሺህ 600 ብር ከፍተኛ ዋጋ ተመዝግቦ እንደነበር ካፒታል መዘገብ ይታወሳል። በንፅፅሩ ዝቅተኛው ዋጋ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ 12 ሺህ 320 ብር ነበር።

CapitalNews

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 1 2018 ዓ.ም ገበያ ላይ ውሏል !!!

በኢትዮጵያ ነፃ ኘሬስ ከ25 ዓመት በላይአገልግለናል !!! -የአርበኞች አደራና የትውልዱ...

ከሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የተላለፈ ጥሪ

በክልላችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያደገ የመጣው የተሳሳተ ስሌት የወለደው...

በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ በከባድ መሳሪያዎች የታገዘ  የተኩስ ልውውጥ ተካሄደ

ለዓለም የንግድ ሰንሰለት እጅግ ስትራቴጂካዊ በሆነው የሆርሙዝ ባህረ ወሽመጥ...

የሲ.ኤን.ኤን መስራች ቴድ ተርነር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የዓለማችን ግዙፍ የዜና አውታር ሲኤንኤን መስራች ቴድ ተርነር በ87...