በኢትዮጵያ የሕይወት መድህን ሽፋን ከ0 ነጥብ 5 በመቶ በታች መሆኑን አንድ ጥናት አመላከተ

Date:

በመድህን ገበያ ልማት ላይ ጥናት ያካሄደውና በደቡብ አፍሪካ ኬፕታውን የሚገኘው የፋይናንስ ቁጥጥር እና ማካተት ማዕከል (ሴንፍሪ)፤ ከአጠቃላይ የኢትዮጵያ መድህን ሽፋን ውስጥ የሕይወት መድህን ድርሻ ከ0 ነጥብ 5 በመቶ በታች መሆኑን አስታውቋል፡፡

ማዕከሉ የኢትዮጵያ የሕይወት መድህን ሽፋን ዝቅተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ያደረግሁት ጥናት ያሳያል ሲል ገልጿል።

ጥናቱ የገበያ ተለዋዋጭነትን በጥልቀት ለመረዳት፣ እድሎችን ለማጉላት እና በዘርፉ ውስጥ እድገትን እና ተሳትፎን የሚገድቡ ችግሮችን ለመለየት ያለመ ነው ተብሏል።

የምርምር ተቋሙ በአደረገው ጥናት በአሁኑ ወቅት ከ7 እስከ 10 በመቶ የሚሆኑ አዋቂዎች ማንኛውንም አይነት መደበኛ የመድህን አገልግሎት ተጠቃሚዎች እንደሆኑ ገልጿል።

ከእነዚህም ውስጥ የሕይወት መድህን ወይም ኢንሹራንስ ሽፋን ከ0 ነጥብ 5 በመቶ በታች መሆኑን የተቋሙ ቴክኒካል ዳይሬክተር ክሪስቲን ሁጋርድ ለአሐዱ ሬዲዮ ተናግረዋል። ሆኖም ቴክኒካል ዳይሬክተሯ የኢንሹራንስ ሰጪዎች ቁጥር ባለፉት 20 ዓመታት በእጥፍ ጨምሯል ብለዋል።

በዚህም የኢንሹራንስ ገበያው በከፍተኛ ደረጃ እያደገ እንደሚገኝ ጠቁመዋል። ነገር ግን ሽፋኑ ከሀገሪቱ አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት ዕድገት አንፃር በጣም ዝቅተኛ እንደሆነ ገልጸዋል።

የኢንሹራንስ ገበያው በሞተር ኢንሹራንስ ላይ ከፍተኛ ትኩረት ማድረጉን ያነሱት ቴክኒካል ዳይሬክተሯ፤ ይህም ከጠቅላላው የኢንሹራንስ አረቦን 55 ነጥብ 8 በመቶውን እንደሚሸፍን ተናግረዋል።

እንደ አቪዬሽን፣ የባህር ሃይል፣ የምህንድስና እና የእሳት አደጋ ያሉ ተቋማት 30 በመቶ ይይዛሉ ያሉት ቴክኒካል ዳይሬክተሯ፤ በታሪክ 85 በመቶ የሚሆኑት የፕሪሚየም ክፍያዎች በዋና መሥሪያ ቤቶች በኩል ተከፍለዋል ብለዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ ከአውሮፓውያኑ 2024-2025 ባለው ጊዜ ውስጥ የኢትዮጵያ አጠቃላይ ኢንሹራንስ 38 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር መድረሱን የብሔራዊ ባንክ መረጃ የሚጠቁም ሲሆን፤ ከዚህም ውስጥ 2 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር የሚሆነውን የሚይዘው የሕይወት ኢንሹራንስ ነው ብሏል፡፡

(አሐዱ ሬዲዮ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...