በወንጀል ድርጊት ስለሚገኘ ንብረትን ጉባዔ እየተካሄደ ነው

Date:


የምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ/ ንብረትን ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብ ወንጀል መከላከል ቡድን 50ኛ የከፍተኛ ሃላፊዎች ጉባዔ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡


በጉባዔው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዓለምጸሐይ ጳውሎስ፣ የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሙሉቀን አማረ እና የቡድኑ ሊቀ መንበር ፍሬዘር አያሌው ተገኝተዋል፡፡


የምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብን ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብ ወንጀል መከላከል ቡድን ዓመታዊ ጉባዔ ከነሐሴ 16 እስከ 24 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።


በዛሬው ዕለት የተጀመረው የቡድኑ ከፍተኛ ሃላፊዎች ጉባዔም የምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብን ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብ ወንጀል መከላከል ቡድን ዓመታዊ ጉባዔ አካል ነው፡፡


በጉባዔው ከአባል ሀገራቱ፣ ከአንድ ታዛቢ ሀገር እና ከሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት የተወጣጡ 1 ሺህ 150 በላይ ተወካዮች በመሳተፍ ላይ ናቸው፡፡


ኢትዮጵያ በቀጣናው በወንጀል ድርጊት የተገኘ ንብረትን ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብ ወንጀል መከላከል ላይ በንቃት እየተሳተፈች እንደምትገኝ በመድረኩ ተነስቷል፡፡


በዘርፉ የሕግ ማሻሻያ ከማድረግ ጀምሮ ከተለያዩ ሀገራት ጋር በትብብርና በቅንጅት እየሰራች መሆኑም ተጠቁሟል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ምንገድ ላይ

(በእውቀቱ ስዩም) በቀደም ከሆነ ቦታ ተነስቼ ወደ አልሆነ ቦታ ስራመድ...

ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነ ኢየሱስ በጡረታ ከኃላፊነታቸው ተሰናበቱ

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያንና የአዲስ አበባ አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ...

አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ አዲስ መግለጫ አወጣች

ታዋቂዋ አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ ለስፖርት ወዳጆችና ለደጋፊዎቿ ወቅታዊ መረጃ...