ቴክኒክና ሞያ ተቋማት ተግባር ተኮር ስልጠናን ከኢንዱስትሪዎች …

Date:

ይህ የተባለው ተግባረዕድ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ፣ ንፋስ ስልክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ፣ ኬፕለር እና ኤስ ኦ ኤስ ችልድረን ቪሌጅስ በጋራ በመሆን ባሰናዱት የስራ አውደ ርዕይ ሲካሄድ ነው፡፡

ኢንዱስትሪውና የሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች ስልጠናዎችን በጋራ መስጠት ከቻሉ ተማሪው በቀላሉ የስራ እድል ተጠቃሚ ይሆናል ተብሏል፡፡

የአዲስ አበባ ተግባረዕድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ምክትል ዲን አቶ መሃሙድ ጠይብ ከሙያ ተቋማት ተመርቀው የሚወጡ ተማሪዎች በተማሩበት ዘርፍ የተሻለ ክህሎትና ብቃት ይዘው መመረቅ አለባቸው ይላሉ፡፡

ይህ የሚሆነው ደግሞ ኢንዱስትሪውና የትምህርት ተቋማቱ ተቀራርበው ሲሰሩ ነው ያሉን አቶ መሃሙድ በሙያ ተቋማት የሚሰለጥን አንድ ተማሪ ውጤት የሚሰጠው ከትምህርት ቤቱ ብቻ ሳይሆን የተግባር ልምምድ ከሰራበት አንዱስትሪ ጭምር ነው፡፡

አሁን እንደ ከተማ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች በሚገባ እንዲሰሩ ዘርፍ እየመረጡ በተወሰነ የስልጠና መስክ ትኩረት አድርገው እንዲሰሩ እየተሞከረ ነው ተቋማቱ በዚህ መንገድ መስራታቸው የበለጠ ውጤታማ እንዲሆኑ ያደርጋል ብለዋል፡፡

የኬፕለር የአካዳሚክስና የፕሮግራም ማናረጅ ፍሬሂወት የማነ ተግባረ ዕድ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅን ጨምሮ ከሌሎችም ኮሎጆች ጋር ተማሪዎችን ለስራ ብቁ ለማድረግ በሚደረገው እንቅስቃሴ ስልጠናዎችን በመስጠት እንደሚያግዙ ነግረውናል፡፡

ተማሪዎቹ ስራ እንዲያገኙ ከኢንዱስትሪዎች ጋር እንዲገናኙ እያደረጉ መሆኑን ያስረዱት ፍሬሕይወት የማነ ዘንድሮ ለ4 ተኛ ጊዜ የስራ አውደ ርዕይ ተዘጋጅቶ 70 ድርጅቶች መሳተፋቸውን ጠቅሰዋል፡፡

የትምህርት ተቋማት በየጊዜው ትምህርት ዓይነቶች መገምገም አለባቸው ባለፉት 4 ጊዜያት ባደረጉት የስራ አውደ ርዕይ አንዳንድ የትምህርት ዓይነቶች ከመንግስት መስሪያ ቤት ውጪ በኢንዱስትሪው ዘርፍ ስራ ለማግኘት እንደማይቻል ተመልክተናል ብለዋል፡፡

ሸገር 102.1

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...