በዕውቀቱ በታላቁ ዓለም አቀፍ ፌስቲቫል ላይ ተመረጠ

Date:

ዝነኛው ደራሲና ገጣሚ በዕውቀቱ ሥዩም በስፔን ባርሴሎና በሚካሄደው 41ኛው ዓለም አቀፍ የግጥም ፌስቲቫል ላይ ግጥሞቹን  እንዲያቀርብ  ተጋብዟል።

ይህ ታላቅ ፌስቲቫል ከግንቦት 6 እስከ 13 ቀን 2018 ዓ.ም. የሚቆይ ሲሆን፣ በዕውቀቱ ግንቦት 13 ቀን በታሪካዊውና እጅግ ውብ በሆነው ‘ፓላው ዴ ላ ሙዚካ ካታላና’ አዳራሽ በሚካሄደው የመዝጊያ ሥነ-ሥርዓት ላይ ግጥሞቹን ለዓለም ያሰማል።

ገጣሚው በዚህ መድረክ ከተለያዩ አህጉራት ከተመረጡ 7 ታዋቂ ገጣሚዎች ጋር በመሆን የኢትዮጵያን ሥነ-ጽሑፋዊ ለዛ በዓለም መድረክ ላይ ያስመሰክራል።

የባርሴሎና ዓለም አቀፍ የግጥም ፌስቲቫል እ.ኤ.አ ከ1985 ጀምሮ በየዓመቱ የሚካሄድና በዓለም ላይ ካሉ ጥንታዊና ዝነኛ የግጥም መድረኮች አንዱ ነው።

ፌስቲቫሉ በካታሎኒያ ባህል ውስጥ ትልቅ ቦታ ያለው ሲሆን፣ ግጥም ከሙዚቃ፣ ከዕይታ ጥበብና ከቪዲዮ ጋር ተቀናጅቶ የሚቀርብበት ልዩ ጥበባዊ ድግስ ነው።

በዕውቀቱ ሥዩም የግጥም ስራዎቹን የሚያቀርብበት ‘ፓላው ዴ ላ ሙዚካ ካታላና’ በራሱ በዩኔስኮ  የዓለም ቅርስነት የተመዘገበ አስደናቂ ሕንፃ ሲሆን፣ እንዲህ ባለው ታሪካዊ ቦታ ላይ የኢትዮጵያ ዜማ መሰማቱ የጥበብ ድንበር ተሻጋሪነትን ያሳያል።

ይህ ዝግጅት የኢትዮጵያን ሥነ-ጽሑፍ ከዓለም አቀፍ አዝማሚያዎች ጋር የሚያስተሳስር ከመሆኑም በላይ፣ በዕውቀቱ በሳቅና በቁም ነገር የታጀቡ ግጥሞቹን ለዓለም በማካፈል የአገራችንን ገጽታ በበጎ ጎኑ የሚያስተዋውቅበት ታላቅ አጋጣሚ ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...