እስራኤል እና አሜሪካ በከፍተኛ ሁኔታ ትኩረት ያደረጉት በአየር ላይ ባላቸው የበላይነት ሲሆን፣ ኢራን ደግሞ ረጅም ርቀትን ተጉዘው በሚያጠቁ ሚሳዔሎች ላይ ነው።
ባለፉት ጥቂት ቀናትም በመቶዎች የሚቆጠሩ የኢራን ሚሳዔሎች እስራኤልን ዒላማ አድርገው ተተኩሰዋል።
እስራኤል ደግሞ በዋናነት ትኩረት የሰጠችው እነዚህን የኢራንን የሚሳዔል ማስወንጨፊያ ማዕከላትን በማውደም ላይ ነው። በዚህም ምክንያት አሁን የእስራኤል አየር ኃይል በአብዛኛው የአገሪቱ የአየር ክልል ላይ የበላይነትን እንደያዘ እየተነገረ ነው።
ምንም እንኳን የኢራን የሚሳዔል ማዕከላት ጉዳት ቢደርስባቸውም አሁንም በእስራኤል ላይ ጥቃት እየፈጸመች ነው።በዚህም የተለያዩ የእስራኤል ክፍሎች ዒላማ ሆነዋል።
ለመሆኑ ኢራን ምን ዓይነት ሚሳዔሎች አሏት? ምን ያህል ርቀትስ መጓዝ ይችላሉ?
