በድሬዳዋ ከ47 የምርጫ ክልሎች ውስጥ ብልፅግና ፓርቲ በ32ቱ ብቻውን ይወዳደራል

Date:

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋ ያደረገው የ7ተኛው ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ የዕጩዎች ዝርዝር ሰነድ እንደሚያሳየው፣ የድሬዳዋ ከተማ ምክር ቤት ካሉት 47 የምርጫ ክልሎች ውስጥ፣ በ32ቱ ብልፅግና ፓርቲ ብቻውን ይወዳደራል።

የድሬዳዋ ከተማ ምክር ቤት በአጠቃላይ ካሉት 189 መቀመጫዎች ብልፅግና ፓርቲ ለ161ዱ ዕጩዎችን ያቀረበ ሲሆን፣ ከነዚህ ውስጥ 92ቱ ያለምንም ተፎካካሪ የሚወዳደሩ ናቸው። በዚህም ብልፅግና ፓርቲ 48.7 በመቶ የሚሆነውን የድሬዳዋ ከተማ ምክር ቤት ወንበሮች እንደሚቆጣጠር አስቀድሞ መገመት ተችሏል።

ከ47ቱ የምርጫ ክልሎች ውስጥ በ15ቱ፣ ስምንት ተቃዋሚ ፓርቲዎች በድምሩ 47 ዕጩዎችን ማቅረብ ሲችሉ፣ አንድ የግል ተወዳዳሪም በ02 ቀበሌ የምርጫ ክልል ይወዳደራል።

ለክልል ምክር ቤቶች በአንድ የምርጫ ክልል ከአንድ በላይ የምክር ቤት መቀመጫዎች ውድድር እንደሚደረግባቸው ይታወቃል። [ምርጫ 2018 – ኢትዮጵያ ኢንሳይደር]

ምርጫ2018 #EthiopiaElection

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ቱርክ ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ የእስር ማዘዣ አወጣች

ቱርክ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ ዓለም አቀፍ...

በመቀለ የሚካሄደው የአሸንዳ በዓል የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ተሰረዘ

በትግራይ በርካታ ታዳሚ በሚገኝበት በየዓመቱ የሚከበረው የአሸንዳ ባህላዊ በዓል...

የኢትዮጵያ ፖስታ 3 ሺሕ የሚጠጉ ቅርንጫፎቹን ወደ ባንክ ኤጀንትነት ለመቀየር እንቅስቃሴ ጀመረ

የኢትዮጵያ ፖስታ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ 3 ሺሕ በሚጠጉ ቅርንጫፎቹ...

«ግብጽ ዛቻውን አቁማ ወደ ድርድር ትግባ!»

ታዋቂው የአፍሪካ ፖለቲካ ተንታኝ ዶ/ር ዴቪድ ማትሳንጋ ግብጽ በኢትዮጵያ...