ብሄራዊ ባንክ፣ ፍቃድ የሌላቸውን የገንዘብ አስተላላፊ ኩባንያዎችን እና ሌሎች ሕገወጥ የሐዋላ አስተላላፊዎችን መጠቀም አገር ውስጥ የሚገኙ የሐዋላ ተቀባዮችን ችግር ላይ ይጥላል ሲል ማምሻውን ባወጣው ማሳሰቢያ አስጠነቀቀ።
ባንኩ በውጭ አገር በሚገኙ የሐዋላ አስተላላፊዎች ላይ ብቻ ሳይሆን፣ በአገር ውስጥ “ሕገወጥ የውጭ ምንዛሬ ተቀባዮች” ላይ ርምጃ አየወሠደ መሆኑን ገልጧል።
ውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵይያዊያን ገንዘብ የሚልኩላቸውን ዘመዶቻቸውንና ወዳጆቻቸውን ከእንግልትና ችግር ለመጠበቅ ሕጋዊ አማራጮችን ብቻ እንዲጠቀሙ ባንኩ አሳስቧል። ባንኩ፣ “ሽጌ”፣ “አዱሊስ”፣ “አቫንቴ”፣ “ሬድኸ ሲ”፣ “ወርልድ ዳይሬክት ሊንክ”፣ “ራስማ ፔይ”፣ “ዩኤስ ዋየር”፣ “ዞላ” እና “ታጅ” ለአብነት በአገር ውስጥ ፍቃድ የላቸውም ብሏል።
