ቻይናና አሜሪካ ለተጨማሪ ዘጠና ቀናት ታሪፍ ላለመጨመር ተስማምትዋል ተባለ። በዓለም በባለግዙፍ ኢኮኖሚዎቹ መካከል የተፈጠረው የታሪፍ ውጥረት አደጋ ይዞ ይመጣል በሚል ውይይቶች ሲደረጉ ቆይተዋል።
ቤይጂንግና ዋሽንግተን ተጨማሪ ታሪፍ እርስበርስ ”ሊጣጣሉ ” የመጨረሻው ቀን ላይ ደርሰው ነበር።
ለተጨማሪ ሶስት ወራት ታሪፍን ላለመጣል አስቀምጠውት የነበረውን ቀነ ገደብ አራዘሙት የሚል መረጃ ቅድሚያ በሲ ኤን ቢ ሲ በኩል የወጣ ሲሆን ይህም የዓለምን ኢኮኖሚ በተወሰነ መጠን ያረጋጋዋል የሚል ተስፋ ተጥሎበታል።
አገራቱ ባይስማሙ ኖሮ አሜሪካ ከቻይና በምታስገባቸው ምርቶች ላይ ከ30 በመቶ ወደ 64 በመቶ ታርፉን ከፍ ለማድረግ ትገደድ ነበር።
ቻይና በአሜሪካ ላይ ምን ያህል ታሪፍ ልትጥል እንደምትችል ግን የታወቀ ነገር አልነበርም።
በእርግጥ በአሁኑ ሰዓት ቤይጂንግ ከዋሽንግተን በምታስገባቸው ምርቶች ላይ አስር በመቶ ታሪፍ እንደጣለች ይታወቃል።
ከዋይት ሀውስ ወጣ የተባው የተስፋ መረጃ ይፋ የሆነው ዶናልድ ትራምፕ ከ90 በላይ አገራት ላይ ታሪፍ በጣሉ ማግስት ነው።
ሲ ኤን ኤንና ሲ ኤን ቢ ሲ ኒውስ ዘግበውታል።
