አማዞን በ3 ወራት 30ሺ ሠራተኞችን መቀነሱ ተነገረ

Date:

የአሜሪካው አማዞን 16,000 ሠራተኞችን እንደሚቀንስ ረቡዕ ማረጋገጡን ኒውስማክስ ዘገበ፡፡

ኩባንያው ካለፈው ጥቅምት ወር ጀምሮ የ30 ሺ ገደማ የሠራተኞች ቅነሳ ዕቅዱን ያጠናቀቀ ሲሆን፤ ከዚህ በኋላ ተጨማሪ ቅነሳ ስለመኖሩ የገለጸው ነገር የለም ተብሏል፡፡

1.58 ሚሊዮን ሰራተኞች ላሉት አማዞን፣ የ30 ሺ ሠራተኞች ቅነሳ ከጠቅላላ የሰው ሃይሉ 10 በመቶውን የሚወክል ነው፡፡

ባለፈው ጥቅምት ወር ኩባንያው 14 ሺ ሠራተኞችን የቀነሰ ሲሆን፤ ለቅነሳው ሰበብ አድርጎ ያቀረበው ሰው ሰራሽ አስተውሎትንና የኩባንያ የአሰራር ባህል መለወጥን እንደነበር ዘገባው አስታውሷል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...