ኢትዮጵያ የቡና መገኛ በመሆኗ ለታሪክና ለሳይንሳዊ አስተዋፅኦ እውቅና ለመስጠት የስያሜ ለውጥ እንዲደረግ ተመራማሪው ሰሎሞን ተክሌ ጥሪ አቅርበዋል።
መገኛው ኢትዮጵያ የሆነው “አረቢካ ቡና” እውነተኛ ምንጩን የሚያንፀባርቅ ስያሜ ያስፈልጋል ብለዋል።
በሌላ በኩል፤ ሌሎች ሀገራት የቡና መገኛ ነን በማለት የሚያቀርቡትን መረጃ አልባ መከራከሪያ ነቅፈዋል።
ተመራማሪው በተጨማሪም የኢትዮጵያ ባለሥልጣናትና ባለድርሻ አካላት ኢትዮጵያ የቡና መገኛ መሆኗን በሳይንሳዊ መንገድ በማረጋገጥ በዩኔስኮ እውቅና ለማስገኘት እንዲሠሩ አሳስበዋል።
“ታሪካዊና ሳይንሳዊ ምንጮች ቡና ከኢትዮጵያ የተገኘ መሆኑን በግልጽ ያሳያሉ” ሲሉ ተመራማሪው ለሀገር ውስጥ ሚዲያ መናገራቸውን ስፑትኒክ ዘግቧል፡፡
