ለ13 ተከታታይ ዓመታት ሳይቋረጥ የታየው “ቤቶች” ድራማ የዕይታ ጊዜውን ሊያጠናቅቅ ነው 

Date:

ለ13 ተከታታይ ዓመታት ያለማቋረጥ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ሲተላለፍ የቆየውና በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅነትን ያተረፈው “ቤቶች” የሲትኮም ድራማ፣ ከተወሰኑ ሳምንታት በኋላ የዕይታ ጊዜውን እንደሚያጠናቅቅ ደራሲ፣ ተዋናይ እና የማስታወቂያ ባለሙያ ጥላሁን ጉግሳ አስታወቀ።

“ቤቶች” ሳይቋረጥ ለረዥም ጊዜ በመታየት ከዓለም ሦስተኛ፣ ከአፍሪካ ደግሞ ሁለተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠ ድንቅ የጥበብ ሥራ እንደሆነ ተዋናዩ ጠቁሟል።

ጥላሁን ጉግሳ እንደገለጸው፣ ድራማው እስካሁን የተጓዘበት የ13 ዓመታት ዕድሜ በቂ በመሆኑ፣ በቀጣይ አዳዲስ ረዥም ተከታታይ ፊልሞችን ለተመልካች ለማቅረብ ሲባል ድራማው እንዲጠናቀቅ ተወስኗል።

ተዋናይ ጥላሁን ጉግሳ ከ”ቤቶች” መጠናቀቅ በኋላ፣ በክፍሎችና በምዕራፍ የተከፋፈለ አዲስ ረጅም ተከታታይ ፊልም ከሁለተኛ ሴት ልጁ ጋር በመሆን ለማቅረብ በዝግጅት ላይ መሆኑን ገልጿል።

ከዚህ በተጨማሪም፣ ከዓመታት በፊት ተሠርቶ ለጥቂት ጊዜ ከታየ በኋላ የታገደውና ስለ አሰብ የባሕር በር አስፈላጊነት የሚተርከው “የባሕር በር” የተሰኘው ፊልሙ በቅርቡ ለዕይታ ይበቃል ብሏል።

ፊልሙ በወቅቱ የታገደው በባለሥልጣናት ትእዛዝ እንደነበር ያስታወሰው ጥላሁን፣ በወቅቱ ከፍተኛ ዛቻና ማስፈራሪያ ደርሶበት እንደነበርም አልሸሸገም።

ያገዱት አካላት ከሥልጣን በመነሳታቸው ፊልሙን ቀደም ብሎ ለማሳየት ቢያስብም፣ የኢትዮጵያና የኤርትራ መንግሥታት ግንኙነት በነበረበት መልካም ሁኔታ ሳቢያ ግንኙነቱን ላለማበላሸት ሲል ፊልሙን ማዘግየቱን ተዋናዩ አስረድቷል።

ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት የባሕር በር ጉዳይ በኢትዮጵያ እንደ አዲስ እየተጠየቀ በመሆኑ፣ ፊልሙን እንደገና ለመልቀቅ መወሰኑን ገልጾአል።

አሐዱ ራድዮ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 1 2018 ዓ.ም ገበያ ላይ ውሏል !!!

በኢትዮጵያ ነፃ ኘሬስ ከ25 ዓመት በላይአገልግለናል !!! -የአርበኞች አደራና የትውልዱ...

ከሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የተላለፈ ጥሪ

በክልላችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያደገ የመጣው የተሳሳተ ስሌት የወለደው...

በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ በከባድ መሳሪያዎች የታገዘ  የተኩስ ልውውጥ ተካሄደ

ለዓለም የንግድ ሰንሰለት እጅግ ስትራቴጂካዊ በሆነው የሆርሙዝ ባህረ ወሽመጥ...

የሲ.ኤን.ኤን መስራች ቴድ ተርነር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የዓለማችን ግዙፍ የዜና አውታር ሲኤንኤን መስራች ቴድ ተርነር በ87...