” አራት ሰው አንድ ቦታ ቀብረናል፤ ከተገደሉት ውስጥ አባትና ልጅ ይገኙበታል ! “

Date:



‎በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣ በምስራቅ ጉራጌ ዞን፣ ምስራቅ መስቃን ወረዳ ኢንሰኖ ነዋሪዎች  እንደተናገሩት፣ በኢንሰኖ ዎቻ ገነነ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ሰኔ 25 ሌሊት የታጠቁ ሃይሎች በድጋሚ በፈፀሙት ድንገተኛ ጥቃት 4 ሰዎች ሲሞቱ 7 ሰዎች መቁሰላቸውን ገልፀዋል።

‎ቃላቸውን የሰጡ ሁለት የኢንሰኖ ወረዳ ነዋሪዎች ” ጥቃቱ በቤተሰብ ፕሮግራም ላይ በተሰባሰቡ የቤተሰብ አባላትና ጎረቤታሞች ላይ ነው የደረሰው ” ብለው  ” ከተገደሉት ውስጥ ሁለቱ አባትና ልጅ ናቸው ” ሲሉ አስረድተዋል።

‎ሌላ የአከባቢው ነዋሪም ” ዛሬ አራት ሰው አንድ ቦታ ቀብረናል፣ ባልና ልጇን አንድ ላይ ያጣች እናት እራሷን ስታ ሆስፒታል ገብታለች ” ሲሉ ስለ ጥቃቱ አሰቃቂነት ተናግረዋል።

‎ስለ ቆሰሉ ሰዎች ብዛት ነዋሪዎቹ ሁለት አይነት ቁጥር ያነሱ ሲሆን ከፊሉ 5 ከፊሉ ደግሞ 7 ናቸው ሲሉ ነው አስረድተዋል።

‎ ከምስራቅ ጉራጌ ዞን እና ከምስራቅ ማስቃን ወረዳ ፖሊስ በጉዳዩ ዙሪያ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደረግነዉ ጥረት ስልክ ባለመስራቱ እና  ባለመነሳቱ ምላሻቸው በዚህ ዘገባ አልተካተተም።

@tikvahethiopia

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ቱርክ ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ የእስር ማዘዣ አወጣች

ቱርክ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ ዓለም አቀፍ...

በመቀለ የሚካሄደው የአሸንዳ በዓል የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ተሰረዘ

በትግራይ በርካታ ታዳሚ በሚገኝበት በየዓመቱ የሚከበረው የአሸንዳ ባህላዊ በዓል...

የኢትዮጵያ ፖስታ 3 ሺሕ የሚጠጉ ቅርንጫፎቹን ወደ ባንክ ኤጀንትነት ለመቀየር እንቅስቃሴ ጀመረ

የኢትዮጵያ ፖስታ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ 3 ሺሕ በሚጠጉ ቅርንጫፎቹ...

«ግብጽ ዛቻውን አቁማ ወደ ድርድር ትግባ!»

ታዋቂው የአፍሪካ ፖለቲካ ተንታኝ ዶ/ር ዴቪድ ማትሳንጋ ግብጽ በኢትዮጵያ...