አርሰናል ሩብ ፍጻሜውን ሲቀላቀል ሊቨርፑል ከውድድሩ ውጭ ሆነ

Date:

በእንግሊዝ ሊግ ካፕ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ አርሰናል ብራይተንን 2 ለ 0 በማሸነፍ ለሩብ ፍጻሜ ደረወሷል።

አሰልጣኝ ሚካኤል አርቴታ 10 ቋሚ ተሰላፊ ተጫዋቾችን ቀይሮ ወደ ሜዳ በገባበት ጨዋታ አሁንም ግብ ሳይቆጠርበት ወጥቷል።

በኢምሬትስ በተደረገው ጨዋታ ንዋኔሪ እና ተቀይሮ የገባው ቡካዮ ሳካ የመድፈኞቹን የማሸነፊያ ግቦች አስቆጥረዋል።

ሊቨርፑል በሜዳው ክሪስታል ፓላስን ባስተናገደበት ጨዋታ 3 ለ 0 ተሸንፎ ከውድድሩ ውጭ ሆኗል።

በአንፊልድ በተደረገው ጨዋታ ኢስማኤል ሳር የፓላስን ሁለቱ ግቦች ሲያስቆጥር የርሚ ፒኖ 3ኛዋን ግብ አስገኝቷል።

ሆላንዳዊው አሰልጣኝ አርን ስሎት ካደረጓቸው ያለፉት ሰባት ጨዋታዎች በስድስቱ ለመሸነፍ ተገደዋል።

በሌሎች ጨዋታዎች ማንችስተር ሲቲ ስዋንሲ ሲቲን 3 ለ 1አሸንፏል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...