አትሌት መሰረት ለ16ሺህ ሴቶች 5ኪ.ሜ. ሩጫ ፈተና አቀረበች

Date:

የሁለት ጊዜ ኦሊምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤቷ የውድድሩ አምባሳደር መሰረት ደፋር ሴቶች አስቀድመው እንዲለማመዱ እና እንዲሮጡ ለማበረታታት ዓመታዊውን የ35 ደቂቃ በታች ፈተና ይፋ አድርጋለች።

ተሳታፊዎች ይህንን ግብ እንዲመቱና በስፖርት የዳበረ ዘመናዊ የአኗኗር ዘይቤን እንዲለማመዱ ለመርዳት፣ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለ4 ተከታታይ ሳምንታት የሚቆይ የስልጠና መርሃ ግብር በማከናወን ላይ ነው።

የውድድሩ መነሻና መድረሻ በቅርቡ እድሳት በተደረገለት ቦሌ አትላስ አካባቢ  ይደረጋል።

ዘንድሮም በተምሳሌት ሴቶች (Icons Women) መሐከል የሩጫ ውድድር የሚከናወን ሲሆን፣ የአሸናፊዎች የገንዘብ ሽልማት በስማቸው ለመረጡት የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ይለገሳል።

ለውድድሩ የተመዘገቡ ተሳታፊዎች ከመጋቢት 2 እስከ 4 ቀን 2018 ከአለም ሲኒማ ጋር ቲሸርታቸውን መውሰድ እንደሚችሉም ታውቋል፡፡

ውድድሩ በሳፋሪኮም፣ ኤም-ፔሳ፣ ዲ.ኬ.ቲ (DKT)፣ ዳሽን ባንከ፣ አከቲቭ (Aktive)፤ የአየርላንድ ኤምባሲ፣ ዩኒሴፍ (UNICEF)፣ ፋብ የውበት ሳሙና፣ ቶፕ ውሃ፣ ህያት ሬጀንሲ፣ ኢቲቪ እና አፍራን ሆስፒታል አጋርነት ይዘጋጃል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...