የቴክኖሎጂ ባለፀጋው ኢሎን መስክ፣ አውሮፓ የወሊድ ምጣኔን ካላሳደገች “ልትጠፋ” እንደምትችል አስጠንቅቀዋል።
የመስክ ማስጠንቀቂያ የተሰማው በስኮትላንድ የወጣውን መረጃ መሰረት በማድረግ ነው።
መረጃው እንደሚያሳየው፣ በ2025 የመጀመሪያ አጋማሽ በስኮትላንድ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከተወለዱት በ34 በመቶ ይበልጣል።
መስክ የህዝብ ቁጥር ራሱን ለመተካት የሚያስፈልገው አማካይ የወሊድ ምጣኔ (replacement rate) 2.1 መሆን አለበት ብሎ ያምናል።
ሆኖም በቅርብ ጊዜ የተደረጉ ጥናቶች ይህ ቁጥር በቂ ላይሆን እንደሚችል እና እስከ 2.7 ድረስ ሊደርስ እንደሚገባ ይጠቁማሉ።
የእንግሊዝ ስታቲስቲክስ ቢሮ እንደገለጸው፣ በ2024 በእንግሊዝ እና ዌልስ የወሊድ ምጣኔ 1.4 ሲሆን፣ በስኮትላንድ ደግሞ 1.3 ነው።
መስክ የወሊድ ምጣኔ ማሽቆልቆል ከአየር ንብረት ለውጥ የበለጠ ለሥልጣኔ አደጋ ነው ሲል በተደጋጋሚ አስጠንቅቋል።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መረጃ እንደሚያሳየው፣ የዓለም አማካይ የወሊድ ምጣኔ ከ50 ዓመታት በላይ ሲያሽቆሎቁል ቆይቷል። በ1970ዎቹ 5 የነበረው ምጣኔ፣ በ2024 ወደ 2.2 ወርዷል።
