ኢራን አሜሪካ ላደረሰችው የአየር ጥቃት አጸፋዊ ምላሽ ሰጠች

Date:

ኢየኢራን አብዮታዊ ዘብ ( አይ አር ጂ ሲ) የባህር እና ኤሮስፔስ ኃይል በጥምረት የሚሳዔል እና ሰው አልባ አውሮፕላን ዘመቻ አድርጎ 85 ወሳኝ የአሜሪካን ጦር ሰፈሮች እንዲሁም ቁልፍ ዒላማዎችን መምታቱን አሳውቋል፡፡

ዋሽንግተን በገሽም ፣ባንዳር አባስ፣እና ሲሪክ ላይ ኃይለኛ ጥቃት በማዕከላዊ ዕዟ በኩል ከፈጸመች በኋላ የተሰነዘረ የቴህራን ጥቃት ነው ፡፡

አይ አር ጂ ሲ በአሜሪካው ፊፍዝ ፍሊት (የጦር ምድብ ) በባህሬን እንዲሁም በአሊ-አል ሳሌም የአየር ኃይል ጦር ሰፈር በኩዌት አደገኛውን ጥቃት ማድረሱን አሳውቋል ፡፡

አሜሪካ ተኩስ አቁምን በመጣሷ የተሰጠ ምላሽ ነው ያለችው ቴህራን አሁንም እርምጃዋን አጠናክራ ልትቀጥል እንደምትችል አስጠንቅቃለች ፡፡

ምንም እንኳን አሜሪካ በወታደራዊ መሰረተ ልማቶች ላይ ጥቃት አድርሻለሁ ብትልም ፤ኢራን ጉዳቱ ያን ያህል አልበረታብኝም በሚል አስተባብላለች፡፡

በባህር ዳርቻዎች ፣ በሆርሞጋን እና ማህሻህር አካባቢዎች ጥቃት መድረሱም ይፋ ሆኗል ፡፡

አሜሪካ እና ኢራን ዳግም ወደ ውጥረት ውስጥ መግባታቸው የአያቶላህ አሊ ኻሚኒን የሽኝት ስነ -ስርዓት ጥቁር ጥላ ያጠላበታልም ተብሏል ፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ከፖለቲካ ራሳቸውን አገለሉ

ላለፉት 5 አስቸጋሪና ፈታኝ ዓመታት (ከ2014 እስከ 2018 ዓ.ም)...

ንባብ ለሕይወት  እየመጣ ነው !!!

በንባብ ለሕይወት ፕሮጀክትና በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት አዘጋጅነት የሚካሄደው...

“ወጣቱን በጉልበት እያፈሱ ወደ ጦርነት እየነዱት ነው!”

"ሰላም፣ ዴሞክራሲና ልማት በትግራይ፦ የመገናኛ ብዙኃን እና የማኅበረሰብ አንቂዎች...