ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ኤክስፖን ልታዘጋጅ ነው

Date:

ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂ ዘርፍ ያላትን አቅም ለአለም ለማሳየት እና የአፍሪካ የቴክኖሎጂ ማዕከል ለመሆን የሚያስችላትን ጉዞ ያጠናክራል የተባዉ አለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ኤክስፖ (ETEX 2025) በአዲስ አበባ  ልታዘጋጅ መሆኑ ተገለፀ።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (INSA) እና የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት (EAll) በጋራ የሚያዘጋጁት ይህ ኤክስፖ ከ100 በላይ የሀገር ውስጥና አለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ድርጅቶች፣ ከ50 በላይ ስታርታፖች እንዲሁም ከ10 ሺህ በላይ ሰዎች የሚሳተፉበት ነው።

ከግንቦት 8 እስከ 10 ፤2017 ዓ.ም. በሚካሄደዉ ኤክስፖው ላይ የቴክኖሎጂ ውጤቶችና አገልግሎቶች የሚቀርቡበት ዓውደ ርዕይ፣ ወርክሾፖች፣ ጥናታዊ ወረቀቶች፣ የፓናል ውይይቶች፣ የሃካቶን እና የ AI ሮቦቲክስ ውድድሮች እንደሚቀርብ ካፒታል ሰምቷል።

ኤክስፖው በሳይበር ደህንነት፣ በሰው ሰራሽ አስተውሎት(Al)፣ ፋይናንስ ቴክኖሎጂ (FinTech)፣ ስማርት ከተማ (Smart City)፣ እንዲሁም በቴክኖሎጂ ትምህርት (Tech Education) ላይ እንደሚያተኩር ተነግሯል።

CapitalNews

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...