ኢትዮጵያና ሞሮኮ የሴቶችን የግብርና ተሳትፎ ለማሳደግ የጋራ ኤግዚቢሽን ከፈቱ

Date:

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ከሚገኘው የሞሮኮ መንግስት ኤምባሲ ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ የመጀመሪያውን የኢትዮጵያ–ሞሮኮ ማህበራዊና ትብብራዊ ኢኮኖሚ እና ደቡብ–ደቡብ ትብብር ኤግዚቢሽን በይፋ ከፍተዋል።

ለሁለት ቀናት በሚቆየው በዚህ ኤግዚቢሽን በሴት ሥራ ፈጣሪዎች ብቻ የሚመረቱ የግብርና ምርቶች እየታዩ ሲሆን፣ በዘርፉ ያላቸውን ወሳኝ ሚና ያጎላል። ዝግጅቱ የደቡብ–ደቡብ ትብብርን ለማጠናከር፣ አካታች እና ዘላቂ ልማትን ለማስፋፋት እንዲሁም ሴቶች በግብርናው ዘርፍ ያላቸውን የለውጥ ሚና ለማክበር ያለመ ነው።

በመክፈቻ ስነ ስርዓቱ ላይ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር እርጎጌ ተስፋዬ፣ በኢትዮጵያ እና በሞሮኮ መካከል ያለውን ጥልቅ ባህላዊና ታሪካዊ ትስስር አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ አቅም ማጎልበት ዋነኛ አጀንዳው አድርጎ እንደወሰደው የገለፁት ሚኒስትሯ፣ በአሁኑ ወቅት ከ8 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን ሴቶች በተለያዩ ህብረት ስራ ማህበራት ስር ተደራጅተው እንደሚገኙም አስታውቀዋል።

የሞሮኮ አምባሳደር ማዳም ነዚሃ አሎይ መሃመዲን በበኩላቸው፥ ሞሮኮ ኢትዮጵያን እንደ ስትራቴጂካዊ አጋር እንደምትመለከት ገልፀው፣ የሁለቱ ሀገራት ትብብር ለአፍሪካ ልማት አርአያ እንዲሆን ምኞታቸውን አሳውቀዋል።

የኢትዮጵያ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር እርጎጌ ተስፋዬ በበኩላቸው፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ጥልቅ ግንኙነት አሞካሽተዋል። ግብርና የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ አከርካሪ ሲሆን ሴቶችም “የለውጥ ዘርን የሚዘሩበት” ዘርፍ መሆኑን ገልፀዋል።

ሁለቱም ሀገራት ለደቡብ-ደቡብ ትብብር ያላቸውን ጽኑ ቁርጠኝነት ያረጋገጡ ሲሆን፣ ይህ ሳምንት ለሴቶች አቅም ማጎልበት አዲስ ምዕራፍ መጀመሪያ እንደሆነ ተገልጿል።

CapitalNews

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...