ኢትዮጵያና አሜሪካ ሕገ ወጥ የገንዘብ ዝዉዉር ላይ መከሩ

Date:

የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም ሕገ ወጥ ድንበር ተሻጋር የገንዘብ ማስተላለፊያ ግብይቶችን መከላከልና መቆጣጠር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ መክረዋል፡፡

በዚህም በገንዘብ ማስተላለፊያ መንገዶች ላይ በሚደረገው ቁጥጥር ያላቸውን ትብብር ለማጠናክርና የገንዘብ ዝውውሩ በመደበኛ የፋይናንስ ሥርዓት ውስጥ መከናወኑን ማረጋገጥ በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ተወያይተዋል።

በኢትዮጵያ ያለውን የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ይበልጥ ማሻሻል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መምከራቸውንም ባንኩ ለፋና ዲጂታል የላከው መረጃ ያመላክታል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ምንገድ ላይ

(በእውቀቱ ስዩም) በቀደም ከሆነ ቦታ ተነስቼ ወደ አልሆነ ቦታ ስራመድ...

ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነ ኢየሱስ በጡረታ ከኃላፊነታቸው ተሰናበቱ

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያንና የአዲስ አበባ አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ...

አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ አዲስ መግለጫ አወጣች

ታዋቂዋ አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ ለስፖርት ወዳጆችና ለደጋፊዎቿ ወቅታዊ መረጃ...