እስራኤል 8ሺ ኢትዮጵያውያን ጥገኝነት ጠያቂዎችን ልታባርር ነው

Date:

​እንደ Middle East Eye ዘገባ፣ የእስራኤል መንግሥት በመጪው ሚያዝያ ወር በሀገሪቱ የሚገኙ 8,000 ኢትዮጵያውያን ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ አቅዷል።

የሕዝብና ኢሚግሬሽን ባለሥልጣን ከሚያዝያ 9 ቀን 2018 ዓ.ም  ጀምሮ ስደተኞቹን በቁጥጥር ስር ማዋልና ማባረር እንደሚጀምር ታውቋል።

​የእርዳታ ድርጅቶች እንደሚገልጹት፣ ሊባረሩ ካሉት መካከል 1,000 ያህሉ ከትግራይ ክልል የመጡ ናቸው።

የእስራኤል ጠቅላይ ፍርድ ቤት መንግሥት “አይሁዳዊ አይደሉም” ያላቸውን እነዚህን ስደተኞች እንዲያባርር ፈቅዷል።

​በአሁኑ ወቅት እስራኤል ውስጥ 72,000 ገደማ ጥገኝነት ጠያቂዎች የሚገኙ ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥ 57% የሚሆኑት በድህነት ውስጥ እንደሚኖሩ የ Assaf ድርጅት መረጃ ያመለክታል።

መንግሥት ስደተኞቹን “ህገ-ወጥ ሰርጎ ገቦች” በሚል መፈረጁም ተገልጿል።

ምንጭ፦Middle East Eye

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ምርጫ ለሰላም ግንባታ

ግዮን መጽሔት :-ለኢትዮጵያ ሰላም ምርጫ አማራጭ የሌለው መንገድ ነው።...

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከባለፈው  ዓመት የ130 በመቶ ብልጫ  አተረፈ

መጋቢት 30 በተጠናቀቀው የኩባንያው በጀት ዓመት 15.9 ቢሊዮን ብር...

በዕውቀቱ በታላቁ ዓለም አቀፍ ፌስቲቫል ላይ ተመረጠ

ዝነኛው ደራሲና ገጣሚ በዕውቀቱ ሥዩም በስፔን ባርሴሎና በሚካሄደው 41ኛው...