ከዚህ ቀደም ከተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ተፈናቅለው በደብረብርሃን የመጠለያ ጣቢያ የሚኖሩ ተፈናቃዮች ከ5 ዓመት በላይ እንደሆናቸ እና ቁጥራቸ ከ26,000 በላይ እንደሆነ ሰምተናል፡፡
እነዚህ ተፈናቃዮች በቻይና፣ በወይንሸት፣ እንዲሁም በባቄሎ የመጠለያ ካምፖች ይገኛሉ፡፡
አሁን ደግሞ ከ3,000 በላይ የሚሆኑ ተፈናቃዮች ወደ ወይንሸት ካምፕ መምጣታቸውን ተከትሎ በብዙ መቸገራቸውን ከተፈናቃዮች ሰምተናል፡፡
አዳዲስ የገቡትን ተፈናቃዮች በምን ምክንያት ወደ ደብረብርሃን ሄዳችሁ ስንል ጠይቀናቸዋል፡፡
እነሱም በነበሩበት ምስራቅ ወለጋ አሁንም የጸጥታ ችግር እንዳለ እና በስጋት መፈናቀላቸውን ነግረውናል፡፡
የምስራቅ ወለጋ ቡሳ ጎኖፋ ወይም የአደጋ ስጋት በበኩሉ አሁን በአካባቢው ለመፈናቀል ምክንያት የሚሆነ ምንም የፀጥታ ስጋት የለም፣ ወደ ደብረብርሃን የሄዱ አዳስ ተፈናቃዮች የሉም ብሏል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….. https://tinyurl.com/y6wncu5p
ሸገር 102.1
