ከአሜሪካ የተባረሩት የደቡብ አፍሪካ አምባሳደር የጀግና አቀባበል ተደረገላቸው

Date:

“ምርጫችን ባይሆንም ወደ ቤት በመመለሳችን ግን አንጸጸትም።…እንደዚህ ዓይነት አቀባበል ሲደረግልን በደቡብ አፍሪካ ነጮች ላይ የዘር ማጥፋት አለ የሚሉ ውሸቶችን ውድቅ እንዳደረግን በወደድን ነበር፤ ነገር ግን በአሜሪካ ይህን ለማሳካት አልቻልንም” ሲሉ ኬፕ ታውን ሲደርሱ በደጋፊዎቻቸው ደማቅ አቀባበል የተደረገላቸው አምባሳደር ኢብራሂም ራሱል ተናግረዋል።

“በመጋቢት ወር አጋማሽ ከአሜሪካ እንዲወጡ የተነገራቸው ዲፕሎማቱ፤ ደቡብ አፍሪካ ከአሜሪካ ጋር ከ50 ዓመት በላይ ያስቆጠረ ግንኙነቷን ‘ማስተካከልና እንደገና መገንባት’ እንዳለባት ተናግረዋል። ግንኙነቱ መጠገን ያለበት ግን ‘የደቡብ አፍሪካን እሴቶች አሳልፎ በመስጠት’ እንዳልሆነ አጽንኦት ሰጥተዋል።

“ፍልስጤማውያንን መስዋዕት ማድረግ የለብንም። ብሪክስን አንተውም። ከቻይና ጋር ያለንን ግንኙነት አናቆምም። ከአሜሪካ ጋር ያለንን አጋርነትም አንተውም። መታገል ይኖርብናል፤ ክብራችንን ግን መጠበቅ አለብን” ብለዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...