ከፍተኛ ንፋስና በረዶ በቢሾፍቱ የአበባና ፍራፍሬ እርሻዎች ላይ ከባድ ጉዳት አደረሰ

Date:

በኦሮሚያ ክልል ቢሾፍቱ ከተማ በደረሰው ከፍተኛ ንፋስና በረዶ የተቀላቀለበት ከባድ ዝናብ፣ በአካባቢው በሚገኙ የአበባና የፍራፍሬ እርሻዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደረሰ። ይህ ያልተጠበቀ የአየር ሁኔታ በተለይ ለዘርፉ አምራቾች ከፍተኛ ኪሳራ አስከትሏል።

በዚህም ከትናንት በስቲያ (ሰኞ) ሁለት ዋና ዋና እርሻዎች ላይ የሚገኙት ግሪን ሐውሶች ሙሉ በሙሉ መዉደማቸዉን ለካፒታል የደረሰው መረጃ ያመለክታል።

ከእነዚህ ሁለት እርሻዎች በተጨማሪ፣ ሌሎች ስምንት የሚሆኑ እርሻዎችም ከፍተኛ የሚባል ጉዳት እንደደረሰባቸው ተጠቁሟል ።

በደረሰው አደጋ ምክንያት በአካባቢው የነበረው የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቋርጦ የነበረ ሲሆን፣ ይህ ደግሞ የእርሻ ስራዎችን ይበልጥ ተፅዕኖ ዉስጥ እንደሚጥለው ተገልጿል ።

በአደጋው የተጎዱት አምራቾች አሁን ባለው ሁኔታ ውስጥ ተጨማሪ ጫናዎች እንዳሉባቸው ገልጸዋል። በተለይም በቀጣይ ወራቶች ዉስጥ ወደ ስራ ካልተመለሱ አሁን በባንክ ላይ ያለባቸው ብድር እና ለመንግስት የሚከፍሉት ግብር ከፍተኛ ጫና እንደሚሆናቸው አስረድተዋል።

ይህን ተከትሎ በፍጥነት ወደ ስራ ካልተመለሱ እነዚህን ግዴታዎች ለመወጣት እንደሚቸገሩ እና ተጨማሪ ኪሳራ እንደሚደርስባቸው ስጋታቸውን ለካፒታል ገልጸዋል። በእርሻ ማሳዎች ላይ አሁን የደረሰው ጉዳት መጠን ለማወቅ ዝርዝር ጉዳዮች እየተጣሩ እንደሚገኝ ለመረዳት ተችሏል።

CapitalNews

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የተፈናቀሉ ዜጎች በተጠለሉበት አካባቢ በቋሚነት መኖር የሚያስችላቸው 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የዳሰነች ወረዳ ከበኦሞ...

ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 11ኛውን የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በደብረ ብርሃን ከተማ አስመረቀ

ታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ...

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...