Update
የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ከሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በቱርክ ኢስታንቡል ተገናኝተው ለመነጋገር ፈቃደኛ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ፕሬዝዳንቱ በኤክስ ገጻቸው ሩስያ ለቀጥታ የሰላም ንግግሮች ያቀረበችውን ሀሳብ በደስታ በመቀበል ነገር ግን ድርድር ከመጀመሩ በፊት የተኩስ አቁም መኖር እንዳለበት አሳስበዋል።
የሩስያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን የቀጥታ ውይይት ለመጀመር ያቀረቡትን ጥሪ በጎ ምልክት መሆኑንም ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ጠቅሰዋል።
ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ ሐሙስ ዕለት በቱርክ ኢስታንቡል ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲንን እጠብቃለሁ ብለዋል።
መላው ዓለም ይህን ለረጅም ጊዜ ሲጠብቀው ቆይቷል ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ ሆኖም ግን ማንኛውንም ግጭት ለማስቆም የመጀመሪያው እርምጃ መሆን ያለበት የተኩስ አቁም ስምምነት ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡
