በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የመጀመሪያዋ ሴት ሠራተኛ በመሆን ከቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ጀምሮ በተለያዩ መምሪያዎች ለረዥም ዓመታት በቅንነትና በታማኝነት ሲያገለግሉ ኖረው እድሜያቸው ለጡረታ ሲደርስ በክብር የተሸኙት ክብርት ወ/ሮ ትርንጎ በትረ ባደረባቸው ሕመም ምክንያት በጸበልና በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ግንቦት 27 ቀን 2018 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል፡፡
ዛሬ ሰኔ 4 ቀን 2018 ዓ.ም. ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አስከሬናቸው ከሰሜን አሜሪካ አቀባበል ተደርጓል፤ የቀብራቸው ሥነ ሥርዓትም ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የመምሪያ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች፣ የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎችና ሠራተኞች እንዲሁም ወዳጅ ዘመዶቻቸው በሚገኙበት በመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ዓርብ ሰኔ 5 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ይፈጸማል ፡፡
ልጆቻቸውና ቤተሰቦቻቸው
