በዙምባብዌ ሀራሬ እየተካሄደ በሚገኘው የአፍሪካ የባህል ስፖርቶች እና ጨዋታዎች ኮንፌዴሬሽን አመታዊው ጉባዔ ላይ እየተሳተፉት የሚገኙት የኢትዮጵያ ባህል ስፖርቶች ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ህይወት መሀመድ የኮንፌዴሬሽኑ ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው በዛሬው ዕለት ተሾመዋል።
የሀገራችን 11 ባህል ስፖርቶች የውድድር ህግና ደንብ ወጥቶላቸው አመታዊ ውድድሮች እየተደረጉ ይገኛል።
በሀገር ውስጥ ስፖርቱንና ባህሉን ለማስፋፋት የተሰራው ጥሩ ስራ ፌደሬሽኑን በአህጉራዊ መድረክ ተቀባይነት እንዲኖረው ከማስቻሉም በላይ በአመራርነት ደረጃ ወ/ሮ ህይወት መመረጣቸው በአፍሪካ መደረክ የኢትዮጵያን ስፖርቶች ለማስተዋወቅ ትልቅ አቅም እንደሚፈጥረለት ይታመናል።
(ባህልና ስፖርት ሚ/ር)
