ዛሬ የዓለም አፈር ቀን ነው፤ አፈራችሁን ጠብቁ ከአፈር የተሰራን፣ ወደ አፈር የምንመለስ ነን

Date:

ዛሬ ዓለም የአፈር ቀን ያከብራል። ያለ አፈር ሀገር የለም። በቅንጡ ግንባታዎች መኖር የምንችለው አፈር ሲኖር ነው። የመስታወት ህንፃዎቻችን ያለ አፈር አያኖሩንም። አፈር ነን፤ በገዛ ወገናችን እንጨክናለን ስለ አፈር ግድ አይሰጠንም። ለዚህ ነው የአፈር ቀን ብሎ ማክበር ያስፈለገው።

የዚህ ዓመት መሪ ቃል “Healthy Soils for Healthy Cities,” ከተሜነት ከአፈር ጉዳይ መራቅ መስሎናል። ግን ለጤናማ ከተማ ጤናማ አፈር ግድ ነው። ብልሹ ሥልጣኔ ማለት በአፈር ላይ አለመሰልጠን ነው። ለልጆቻችን ቤት ለማውረስ እንደክማለን። አፈር በሌላት ሀገር ቤት ከንቱ ነው። ይልቁንስ አፈር ያለው ሀገር እናውርሳቸው ቤቱን እነሱ ይሰሩታል።

ስለ አፈር ስለማንነጋገር “አፈር የበላ” የምንለውን ዓይነት ህይወት እንኖራለን። እንኳን ምድሩ እኛ ከአፈር የተሰራን መሆኑን እንረሳለን። ከ95 በመቶ በላይ የሚሆነው ምግባችን በአፈር የሚገኝ ነው።

ምን እንደምናውቅ አናውቅም። ባለ ከረቫቱ ሁሉ ወንዝ ጠላ መስሎ ሲሄድ አይገርመውም። በአየር ንብረት ለውጥ እና በሰው ልጅ እንቅስቃሴ አፈሩ እየተበላሸ ነው። ግን ይሄ አጀንዳ “አፈር አፈር አለኝ” ከሚል ሰው ጋር በአንድ አፈር እየኖርን ፈተናችን ከብዷል። በአፈር መሸርሸር ጦስ የተፈጥሮ ሚዛን ይዛባል። ሥነ ሕይወት ያጠፋል። በምግብ ውስጥ የቪታሚኖች እና ንጥረ ነገሮች መጠንን ይቀንሳል።


ዘላቂ የአፈር አስተዳደር ልምዶች፣ የአፈር መሸርሸርን እና ብክለትን ይቀንሳሉ፣ እንዲሁም የውሃ ሰርጎ መግባትን እና ማከማቻን ያሻሽላሉ። የአፈር ብዝኃነትን ይጠብቃሉ፣ ለምነት ያሻሽላሉ፣ እና ለካርቦን ክምችት አስተዋጽኦ ያደርጋሉ፣ ይህም በአየር ንብረት ለውጥ ላይ በሚደረገው ትግል ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ።

የመንግሥታቱ ድርጅት ዕለቱን አስመልክቶ በአወጣው መረጃ ስለ አፈር ስናስብ፣ ሁልጊዜ ማለት ይቻላል ከገጠር እና ከተፈጥሮ ጋር እናያይዛለን። የከተማ አፈርም መሰረታዊ መሆኑን ከግምት ውስጥ ሳናስገባ አናቆምም። ይላል።


ይህ የዓለም የአፈር ቀን 2025 “ጤናማ አፈር ለጤናማ ከተሞች” በሚል መሪ ቃል በከተማ መልክዓ ምድሮች ላይ ያተኩራል። ከአስፋልት በታች፣ ሕንፃዎችና ጎዳናዎች ዘልቀው የሚገቡና አትክልት የሚበቅል ከሆነ የዝናብ ውሃን ለመምጠጥ፣ የሙቀት መጠንን ለመቆጣጠር፣ ካርቦን ለማከማቸት እና የአየር ጥራትን ለማሻሻል የሚረዳ አፈር አለ።

ነገር ግን በሲሚንቶ ሲታሸግ እነዚህን ተግባራት ያጣ ሲሆን ከተሞች ለጎርፍ፣ ለሙቀት መጨመር እና ለብክለት ተጋላጭ ያደርጋቸዋል። አዲስ አበባ ተስፋ እንዳደርግ አድርጋኛለች። የወንዝ ዳርቻዋን ማልማት ጉዳይዋ ሆኗል። የከተማ ነፃ መሬቶች አፈር ለመታደግ የሚያስችል ልማት ለምቶባቸዋል። ያም ሆኖ ገና ስለ አፈር ብዙ መስራት ይጠበቅብናል።

(ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም )

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...