ፈተናው እስካሁን ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በ3 ዙር በኦንላይን እና በወረቀት ከሰኔ 23/2018 ዓ/ም ጀምሮ ተሰጥቷል።
3ኛው ዙር የተፈጥሮ ሳንይስ ተማሪዎች ፈተና ከሐምሌ 1 እስከ 3 ቀን 2018 ዓ.ም ተሰጥቶ ተጠናቋል።
በትግራይ ክልል ለሚገኙ ተማሪዎችም የኦንላይን ፈተናውን በአግባቡ መውሰዳቸው ፈተናውን ያስፈጸሙት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አሳውቀዋል።
በሀገር አቀፉ ፈተና 4ኛው ዙር የማኅበራዊ ሳይንስ ፈተና ከሰኞ ሐምሌ 6 እስከ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ለ3 ተከታታይ ቀናት በወረቀት እና ኮምፒውተር ይሰጣል።
ፈተናው በ5ኛ እና 6ኛ ዙር እስከ ሐምሌ 16 ቀን 2018 ዓ/ም ድረስ (በኮምፒዩተር) ቀጥሎ ፍጻሜውን ያገኛል።
በሌላ በኩል፣ በትግራይ ክልል ውስጥ በወረቀት ፈተናቸውን ላልተፈተኑ ተማሪዎች ከሐምሌ 22 እስከ ሐምሌ 24 ቀን 2018 ዓ/ም ድረስ ይሰጣል።
