የህዝብ ትራንስፖርት የሚሰጡ ወደ ዲጂታል ክፍያ ሊገቡ ነው

Date:

በአዲስ አበባ ከተማ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎች ከ2018 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ዲጂታል የክፍያ ሥርዓት ሊገቡ ነው።

በቢሮው የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ኃላፊ ዳኛቸው ሽፈራው አዲስ አበባ ከወረቀት የተላቀቀ አገልግሎትን ለመገንባት የስማርት ሲቲ ጉዞ ላይ እንደመሆኗ ተቋሙ ዘርፉን ለማዘመን የሚያስችሉ የተለያዩ ዲጂታል አሰራሮችን ጀምሯል ነው ያሉት።

ቢሮው የትራንስፖርት ስርዓቱን በቴክኖሎጂ የማዘመን ስራ በቬሎሲቲና በከተማ አውቶብሶች መጀመሩን ጠቅሰው፤ ተቋማቱ በተለያዩ የዲጂታል አማራጮች አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን ተናግረዋል።

ከ2018 ዓ.ም ጀምሮ የብዙኃን ትራንስፖርት የሚሰጡ የከተማ አውቶብሶችን ጨምሮ በመዲናዋ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ አብዛኞቹ ተሽከርካሪዎች ወደ ዲጂታል ክፍያ እንደሚገቡ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...