የቱርክ ፖሊስ ከ20 ቶን በላይ የተወረሰ ካናቢስ በማቃጠሉ የተነሳ የአንድ ከተማ ነዋሪዎች ያለፍላጎታቸዉ በአደንዛዥ እጽ መነቃቃታቸዉ ተሰማ

Date:

በቱርክ ዲያርባኪር ግዛት ውስጥ በምትገኘው የላይስ ከተማ 25,000 ነዋሪዎች ፖሊሶች 20 ቶን ካናቢስ በከተማው ውስጥ ካቃጠሉ በኋላ ያለፍላጎታቸው በአደንዛዥ እጽ ተነቃቅተዋል፡፡በኤፕሪል 18 የቱርክ ባለስልጣናት ከ 20 ቶን በላይ የተወረሱ ካናቢስ ለማቃጠል ኦፕሬሽን አድርገዋል፡፡ ይህም በሰፈሩ ውስጥ ያለው አየር በአደንዛዥ ጭስ እንዲወጠር አድርጓል ።

ቢያንስ ለአምስት ቀናት ሰዎች እንደ መስከር እና እንደ መፍዘዝ፣ ማቅለሽለሽ እና ቅዠቶች ያሉ ምልክቶችን በመፍራት መስኮቶቻቸውን ክፍት መተው እና ከቤት ለመውጣት አልቻሉም። በ10 ቢሊዮን የቱርክ ሊራ ወይም 261 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የሚገመተው ካናቢስ 20 ቶን 766 ኪሎ 679 ግራም የሚመዝን ሲሆን በ2023 እና 2024 ከመላው የዲያርባኪር ግዛት የተያዘ ነዉ፡፡

የአካባቢው ነዋሪ እንደተናገረዉ የእጹ ሽታ ለቀናት ከተማዋን ተቆጣጥሮ ቆይቷል ብሏል። መስኮቶቻችንን መክፈት አልቻልንም። ልጆቻችን ታመሙ፣ ያለማቋረጥ ወደ ሆስፒታል ሲንሄድ ነበር በማለት አክሏል፡፡የየሲል ኢልዲዝ ማህበር ሊቀመንበር ያህያ ኦገር እንዳሉት ምንም እንኳን በአደገኛ ዕጾች ላይ በተደረገው ውጊያ በባለሥልጣናቱ የተገኘው ስኬት አስፈላጊ ቢሆንም ካናቢሱ የተወገደበት መንገድ ግን ትክክል አይደለም ብለዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...