መንግስት ለባህል እድገት እና ልማት የሚመድበውን በጀት አቋርጦ ጉዳዩን ለሲቪል ማኅበራት እንዲተው የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ጠይቋል።
“ከግብር ከፋዩ የሚሰበሰብ የህዝብ ሀብት ለአጠቃላይ ሐገራዊ ልማበት ብቻ መዋል አለበት” ያሉት የፓርቲው የስራ አስፈጻሚ አባል አርክቴክት ዮሐንስ መኮንን፣ እንደተናገሩት “መንግስት ከብሔር ቋንቋና ባህል ድጋፍ መዋቅር ሙሉ በሙሉ መውጣት አለበት”
የኢዜማ ስራ አስፈጻሚ አባል አርክቴክት ዮሐንስ አክለውም፤ “ማንነት የማኅበረሰብ እሴት እንጂ የፖለቲካ ጉዳይ አይደለም” ብለዋል፡፡
የቋንቋና የባህል ዕድገት በሲቪል ማኅበራት መመራት እንደሚኖርበት እና የሕብረተሰብ ክፍሎች የራሳቸውን እሴት በራሳቸው መዋጮ መጠበቅ አለባቸው ሲሉ አስረድተዋል።
መንግስት ከማንነትና ከሃይማኖት ጉዳዮች መውጣት እንዳለበት ያሳሰቡት አቶ ዮሐንስ ትኩረቱን በጋራ ሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ ብቻ ማድረግ ይገባዋል ብለዋል።
የታክስ ከፋዩን ሀብት ለተወሰኑ ቡድኖች ፍላጎት ማዋል አድሏዊ አሠራርን ይፈጥራል። ይህ ደግሞ በሀገሪቱ ግጭትን የመፍጠር አቅም አለው ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
ከአሐዱ ራዲዮ
