“የመሪነት ምስል”
የሲዳማ ሀገረ ስብከትና የሀዋሳ ታቦር ፍኖተ ጥበብ መንፈሳዊ ኮሌጅ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ፣ “የመሪነት ምስል” በሚል ርዕስ ያዘጋጁት አዲስ መጽሐፍ መጋቢት 26 ቀን 2018 ዓ.ም በታላቅ ድምቀት ይመረቃል።
የምረቃው ዝርዝር መረጃ፦
መጋቢት 26 ቀን 2018 ዓ.ም (ቅዳሜ)
ከቀኑ 9:00 ሰዓት ጀምሮ
ሀዋሳ በሚገኘው ሴንትራል ያማረች ሆቴል ትልቁ አዳራሽ
ታዳሚዎች፦ በዕለቱ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ የቤተክርስቲያን ሊቃውንት እና የብፁዕነታቸው መንፈሳዊ ልጆች በተገኙበት ይከናወናል።
”መጽሐፍ ፈልጉ አንብቡም” (ኢሳ 34:16)
የሚለውን አምላካዊ ቃል መሠረት በማድረግ፣ በሀዋሳና በአካባቢው የምትገኙ የጥበብ ወዳጆች ሁሉ በዚህ ታላቅ መንፈሳዊና የዕውቀት ግብዣ ላይ እንድትገኙ ተጋብዛችኋል።
