የትራኮማ መከላከያ የመድኃኒት በሰቆጣ እደላ እየተካሄደ ነው

Date:

የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት የትራኮማ መከላከያ የመድሀኒት እደላ ዘመቻ ከሐምሌ 6 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ ለተከታታይ 7 ቀን እየሰጠ እንደሚገኝ አስታውቋል ።

ዘመቻው ማንኛውም በከተማ የሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎችን የሚያሳትፍ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በዘመቻው ከ47ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተደራሽ እንደሚያደርግ ጤና ጽ/ቤቱ አስታውቋል።

ከዘመቻውም ጎን ለጎንም ማንኛውም ከ15 ዓመት በላይ የሆነ የከተማዋ ነዎሪዎች የዓይን ፀጉር መቀልበስ ልየታ እየተሰራ ሲሆን የዓይን ጸጉር መቀልበስ ችግር ያለባችሁ ህክምናው የሚሰጥ መሆኑን አውቀው ህክምናውን እንዲያገኙ ጽ/ቤቱ ጥሪ አቅርቧል።

በተጨማሪም ለዘመቻው መሳካት የከተማው ማህበረሰብ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ሲል ጤና ተቋሙ መጠየቁን ብስራት ከሰቆጣ ከተማ ኮሙኒኬሽን ያገኘው መረጃ ያሳያል::

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...