የኢትዮጵያ ቁጥር 1 ሀብታም የሆኑት ሼክ መሀመድ አል አሙዲ አጠቃላይ ሀብት በጥቂት ወራት ውስጥ ከ2 ቢሊዮን ዶላር በላይ ማደጉን ቢሊየነርስ አፍሪካ ዘግቧል፡፡
እንደዘገባው ኤፕሪል 7 ቀን የሀብታቸው መጠን 5.73 ቢሊዮን ዶላር የነበረ ሲሆን አሁን ግን 7.93 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል፡፡ ይህ የሚያሳየው በጥቂት ወራት ውስጥ 2.2 ቢሊዮን ዶላር ማግኘታቸውን እንደሆነም አስረድቷል፡፡
አልአሙዲ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የሀብታቸው መጠን እያሽቆለቆለ መሄዱ ከተሰማ በኋላ መልሰው ማንሰራራት መጀመራቸውን ነው ዘገባው ያመለከተው፡፡
