የአመራር ክህሎት ላይ ከሰራን ችግሮቻችንን መፍታት እንችላለን

Date:

ለእዚህ መፍትሄ የሆነውን የአመራር ብቃት ማዳበር ላይ ትኩረት አድርጌ እየሰራሁ ነው ሲል The power of international education የተሰኘ አለም አቀፍ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ተናግሯል።

ድርጅቱ ከ15 አመታት በፊት በኢትዮጵያ ስራዎችን መከወን የጀመረ መሆኑ የተነገረ ሲሆን ሴት ተማሪዎችን መደገፍ እና የአመራር ክህሎትን ማስፋት ላይ በትኩረት እንደሚሰራበት ተነግሮለታል።

ተቋሙ ዛሬ ያሰናዳው መርሀ ግብሩም ከአምስት ዓመታት በፊት የጀመረው እና የስነ ተዋልዶ ጤና ላይ የሚሰሩ ባለሙያዎችን የአመራር ክህሎት እንዲኖራቸው ያደረገበት መሆኑን ተናግሯል።

በዚህም መሰረት በጤናው ዘርፍ ላይ የሚሰሩ 148 ተማሪዎችን እያሰለጠነ መሆኑን የተናገረ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ ዛሬ 48 ተማሪዎቹን ብቁ ማድረጉን ተናግሯል።

የአመራር ብቃት እንዲኖራቸው በስልጠና የታገዙት ከኦሮሚያ ክልል እና ከአዲስ አበባ የተውጣጡ ባለሙያዎች ናቸው ሲሉ The power of international education የሰሀራ በስተደቡብ እና የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ኢትዮጵያ ጥላሁን ተናግረዋል።

እነዚህ ተማሪዎች ካሁን በኋላ ወደሚሰሩባቸው ተቋም ሲገቡ ከዚህ ቀደም ይሰሩበት በነበረው የአመራር ሥርዓት፣ ችግሮችን የመፍታት አቅም እና ሌሎች ሂደቶችን በተሻለ መንገድ ተግባራዊ ያደርጋሉ ተብሎ ተስፋ እንደተጣለባች ተናግረዋል።

እንደ ሀገር የአመራር ብቃት እና ክህሎት ላይ እየሰራ ነው ያለው ስራ ጥሩ ቢሆንም የተበጣጠሰ እና በቂ ያልሆነ ነው ተብሏል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ አዲስ መግለጫ አወጣች

ታዋቂዋ አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ ለስፖርት ወዳጆችና ለደጋፊዎቿ ወቅታዊ መረጃ...

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...