የአማራ ክልል ግጭት የጤና አገልግሎትን እያወከ ነዉ

Date:

ኢትዮጵያ ዉስጥ በአማራ ክልል የሚደረገዉ ግጭት የክልሉን የጤና አገልግሎት ክፉኛ ማወኩን ድንበር የለሽ ሐኪሞች (MSF-በፈረንሳይኛ ምሕጻሩ) የተሰኘዉ ግብረ-ሠናይ ድርጅት አስታወቀ።

ዓለም አቀፉ የሕክምና አገልግሎት ድርጅት ዛሬ እንዳስታወቀዉ ግጭቱ ከፍተኛ የመድሐኒት እጥረት አስከትሏልም።

የኢትዮጵያ መንግሥት ኃይላትና  በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፋኖ ታጣቂዎች የሚያደርጉት ግጭት የክልሉን ሕዝብ እንቅስቃሴ በጅጉ አዉኮታል።

ድንበር የለሽ ሐኪሞች እንዳለዉ የካላ-አዛር (Leishmaniasis ወይም ቁንጭር) በሽታንና በእባብ መነደፍ የሚደርሰዉን ሕመም ለማከም የሚረዱ መድሐኒቶች ማግኘት ሲበዛ ከባድ ነዉ።

ድርጅቱ እንዳለዉ በክልሉ የሚገኙ የጤና ተቋማት የሚሰጡት አገልግሎት የቀነሰ ሲሆን በቂ መድሐኒትም የላቸዉም።

በግጭቱ ምክንያት ዓለም አቀፉ የሕክምና ግብረ-ሠናይ ድርጅት MSF ለፅኑ ሕሙማን ይሰጥ የነበረዉን የአምቡላስ ሕክምና አገልግሎት ማቋረጡን አስታዉቋልም።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...