በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የግማሽ ፍጻሜ የመልስ ጨዋታ ፒኤስጂ አርሰናልን በማሸነፍ ለፍጻሜ ማለፉን አረጋግጧል። የፒኤስጂን የማሸነፊያ ግቦች ፋቢያን ሩዪዝ እና አሽራፍ ሃኪሚ ከመረብ አሳርፈዋል።
አርሰናልን ከሽንፈት ያልታደገችዋን ብቸኛ ግብ ደግሞ ቡካዮ ሳካ አስቆጥሯል።
ውጤቱን ተከትሎም ፒኤስጂ አርሰናልን በድምር ውጤት 3 ለ 1 በመርታት ለፍጻሜ ማለፉን አረጋግጧል።
በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የፍጻሜ ጨዋታ ፒኤስጂ ከኢንተርሚላን በአሊያንዝ አሬና ስታዲየም የሚፋለሙ ይሆናል።
