የአፍሪቃ ህብረት ጊኒ ቢሳዎን ከህብረቱ አባልነት አገደ

Date:

ህብረቱ ውሳኔውን ያሳለፈው ፕሬዚዳንት ኡማሮ ሲስኮ ኢምባሎ በመፈንቅለ መንግስት ከስልጣን ከተወገዱ ከሁለት ቀናት በኋላ ነው። የጊኒ ቢሳዎ ወታደራዊ ኃይል ባለፈው ረቡዕ ፕሬዚዳንቱን ከስልጣን ማስወገዱን አስታውቋል።

ሊቀመንበሩ ማህሙድ አሊ የሱፍ እንዳሉት የአፍሪካ ህብረት ጊኒ ቢሳውን ከአባልነቷ በፍጥነት ለማገድ ወስኗል።

በወታደሮች የተፈጸመው መፈልቅለ መንግስት በምዕራብ አፍሪቃዊቷ ሀገር የተደረገው የምርጫ ውጤት በቅርቡ ይፋ ይደረጋል ተብሎ በሚጠበቅበት ወቅት መሆኑን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።

የጊኒ ቢሳዎ ወታደራዊ ሁንታ አዛዡ ጄነራል ሆርታ ንታምን ለአንድ ኦመት የሽግግር መንግስቱ ፕሬዚደንት አድርጎ ሾሟል።

ከስልጣን ከተወገዱ በኋላ በቁጥጥር ስር የነበሩት ፕሬዚዳንት ኡማሮ ሲስኮ ኢምባሎ በድርድር ወደ ሴኔጋል እንዲሸሹ መደረጋቸውን ዘገባው አመልክቷል።

በምርጫው አሸንፌያለሁ የሚሉት የተቃዋሚው ፕሬዚዳንታዊ እጩ ፈርናንዶ ዲያስ “ደህንነታቸው ተጠብቆ”  በሀገሪቱ ውስጥ በአንድ ስፍራ ተደብቀው እንደሚገኙ ለዜና ምንጩ ተናግረዋል።

የምዕራብ አፍሪካ ኢኮኖሚክ ማህበረሰብ (ECOWAS) ሀገሪቱን “ከሁሉም ውሳኔ ሰጪ አካላት” ማገዱ ይታወሳል።ጊኒ ቢሳዎ ከጥቂት አታት ወዲህ የወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ሰለባ የሆነች ሌላዋ ምዕራብ አፍሪቃዊ ሀገር ኾናለች።

DW Amharic

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...