የኢትዮጵያ አዲሱ የቱሪዝም ፖሊሲ

Date:

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የካቲት 23 ቀን 2018 ዓ.ም. ያፀደቀው አዲሱ የቱሪዝም ፖሊሲ፣ የዘርፉን የአገር ውስጥ ጥቅል ምርት (GDP) ድርሻ ከ3 በመቶ ወደ 10 በመቶ ለማሳደግ ማለሙን የቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ።

የቱሪዝም ሚኒስትር ደኤታ አቶ ስለሺ ግርማ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ከ17 ዓመታት በኋላ የተሻሻለው ይህ ፖሊሲ ቀደም ሲል ትኩረት ያልተሰጣቸውን የአገር ውስጥ ቱሪዝም እንዲሁም የኮንፈረንስና ኤግዚቢሽን ዘርፎችን በልዩ ሁኔታ የሚያካትት ነው።

በተለይም እያደገ የመጣውን የኮንፈረንስ ቱሪዝም በሕግና በሥርዓት ለመምራት የሚያስችል ራሱን የቻለ ተቋም ለማቋቋም ፖሊሲው መንገድ የሚከፍት ሲሆን፣ ይህም ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ ታቅዶ የተዘጋጀ ነው።

ፖሊሲው ሚኒስቴሩ ለዘርፉ ልማት የሚያስፈልጉ የሕግ ማዕቀፎችንና ስትራቴጂዎችን ለመንደፍ የነበረበትን የመሠረታዊ ሰነድ እጥረት እንደሚፈታውም ተገልጿል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...