የኢትዮጵያና ታንዛኒያ የጋራ መግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ

Date:



የመግባቢያ ሰነዱን በኢትዮጵያ ምርት ገበያ በኩል የፈረሙት አቶ መርጊያ ባይሳ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሲኾኑ በታንዛኒያ መጋዘን ደረሰኝ ሬገላቶሪ ቦርድ በኩል ደግሞ ሚስተር አቡበከር ሳሉም የታንዛኒያ የመጋዘን ሪጉላቶሪ ሰርቪስ ሥራ አስኪያጅ  ናቸው፡፡

ስምምነቱ ሁለቱ ተቋማት በአቅም ግንባታ፣ በአሰራርና በተሞክሮ ልውውጥ  እንዲሁም በቴክኖሎጂ ሽግግር በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸው መሆኑን አቶ መርጊያ ባይሳ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በፊርማ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ተናግረዋል፡፡

የታንዛኒያ መጋዘን ደረሰኝ ሪጉላቶሪ ቦርድ  አመራር ሚስተር አቡበከር በበኩላቸው የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ለአፍሪካ የግብርና ምርቶች የግብይት አተገባበር ምርጥ ተሞክሮ ያለው በመኾኑ ከተቋሙ ጋራ መሥራት የላቀ ልምድ ለመቅሰምና የተሻለ አቅም ለመገንባት የሚስችል መኾኑንና በአፍሪካም በርስበርስ የገበያ ልውውጦች መስክ የራሱን የጎላ አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል፡፡

የታንዛኒያ መጋዘን ደረሰኝ ሬጉላቶሪ ቦርድ አመራሮች በኢትዮጵያ ምርት ገበያ አካዳሚ ለአራት ቀናት የቆየ ስልጠና  ሲከታተሉ ቆይተው ስልጠናውን መጋቢት 5 ቀን 2017 ዓ.ም አጠናቀዋል፡፡

በስልጠና ማጠቃለያው ላይ አቶ መርጊያ ባይሳ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ምርት ገበያው ባለፉት 17 ዓመታት ያሳካቸውን ምርጥ ተሞክሮዎችንና ያገኛቸው ውጤቶችን ለልዑካን ቡድኑ ገለጻ በማድረግ ውይይት አድርገዋል፡፡

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ በአፍሪካ ቀዳሚው የግብይት ማዕከል መኾኑንና  ዛሬ ላይ ለተፈጠሩ ዘጠኝ የአፍሪካ የግብርና ምርቶች የግብይት ማዕከላት መቋቋም በማማከርና በማሰልጠን ከፍተኛ ድርሻው ተወጥቷል ብለዋል፡፡ 

ሚስተር አቡበከር በበኩላቸው  የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ለአፍሪካ የዘመናዊ ግብይት ሥርዓት ግንባት እያበረከተ ያለውን አስተዋጽኦ አድንቀው፤ በኢትዮጵያ ምርት ገበያ አካዳሚ የተሰጣቸው ስልጠናና በተግባር የተደገፈ ገለጻ ለሀገራቸው የዘመናዊ ግብይት ግንባታ ሥርዓት ቁልፍ መኾኑን አውስተዋል፡፡

ታንዛኒያ ከኢትዮጵያ ምርት ገበያ ስኬቶች የምትቀስማቸው ተሞክሮዎች በጋራ ለመስራት የሚያስችሉን ቁልፍ እሴቶች ናቸው ያሉት አቶ መርጊያ ከዚህ ቀደምም የታንዛኒያ መርከንታል ኤክሰቼንጅ ልዑካን በኢትዮጵ ምርት ገበያ በመገኘት ልምድ መቅሰማቸውንና ዘመናዊ የግብይት ሥርዓት መገንባታቸውን አውስተዋል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...