የዶ/ር ወዳጄነህ መልዕክት ምንድን ነዉ?

Date:

ለብፁዕ ቅዱስ አባታችን አቡነ ኤልያስ
የአርባ ምንጭ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ።

ብፁዕነትዎ በአባትነት ስልጣንዎ “ለዶ/ር ወዳጄነህ አድርሱልኝ” ብለው ያስተላለፉልኝ መልዕክት ደርሶኛል። ብዙ ሰዎች ቪዲዬውን እየላኩልኝ ደጋግሜ አየሁት፣ ሰማሁት።

በመጀመርያ የእኔ ከንቱ ስሞ በእርስዎ ቅዱስ አንደበት በመጠራቱ ብቻ እግዚአብሔርን አመሰግኛለሁ ። እርስዎ ለእኔ ብለው ተናገሩ፣ ጥሪ አቀረቡልኝ እንጂ ያለዚያማ የእኔ አይነቱ ሀጢያተኛ ወደ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቢመጣ ተጨማሪ ሸክም ቢሆንባት እንጂ እርሷን ምን ሊጠቅማት?

ብፁዕ አባታችን! እርስዎ ጥሪውን ያቀረቡበት የእግዚአብሔር ፍቅር ልብ የሚነካ ነበር። እንዲህ እንደርስዎ መለኮታዊ ፍቅር ያደረባችው አባቶች ቢበዙልን ምድራችን ትፈወስ ነበር ብዬ አምናለሁ። ያቀረቡልኝን ጥሪ፣ የመከሩኝን ምክር ስሜታዊ ሳልሆን ከልቤ፣ በፅሞና እንደማስብበት፣ እንደምፀልይበት ቃል እገባሎታለሁ።

እንግዲህ መልዕክትዎ ደጋግሞ ቢደርሰኝ ይቺን ትንሽ ፅሁፍ ልፅፍሎት ደፈርኩኝ።
ይቅር ይበሉኝ።

እግዚአብሔር ይስጥልኝ!
ውለታዎንም ይክፈልልኝ!

ዶ/ር ወዳጄነህ መሐረነ።

(ከዚህ ጋ በተገናኘም ባልተገናኘም መንገድ የተሳሳተ መረጃ የምታቀርቡ አንዳንድ ሚዲያዎች ብትታረሙ መልካም ይመስለኛል።

አንድ ሰው ታዋቂ ሆነ አልሆነ፣ ተማረ አልተማረ ወደ ቤተክርስትያን መምጣቱ፣ መመለሱ ጥቅሙ ለእሱው ነው እንጂ ለንፅህት፣ ቅድስት ቤተ ክርስትያን የሚጨምርላት አንዳች ነገር የለም።

“እከሌ ወደዚህ ተመለሰ” በሚል ያልተረጋገጠ ዜና እግዚአብሔር አይከብርም፣ ሀይማኖትም አይጠቀምም።)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...