ይቺም ሻማ ሰልችታለች!

Date:

በአገራችን ለሚቀጥሉት ብዙ አሥርት ዓመታት ምናልባትም አሁን በሕይወት የምንገኝ ሰዎች በአጠቃላይ ሳናይ የምንሞተው ነገር የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ”ኃላፊነቴን በአግባቡ ስላልተወጣሁ ሥራዬን በፈቃዴ ለቅቄያለሁ፤ ከ’ኔ የተሻለ ሰው ይምራው” የሚለው ነው።

በአርሲ ዞን በኦርቶዶክስ ክርስትና አማኞች እና አብያተ-ክርስትያናት ላይ በተደጋጋሚ ጥቃቶች እየተሰነዘሩ ብዙ ሰው በአሰቃቂ ሁኔታ ሞተ፤ አብያተ-ክርስትያናት እና ቅርሶችም ወደሙ፤ በነዋሪዎቹ ዘንድ ሥጋትና ጥርጣሬ ሰፈነ።

ይሄን ተደጋጋሚ ጥቃት ለማስቀረት የተሠራ ሥራ አለ? ሰላም ማስከበር 100% የክልሉ መንግሥት ሥራ አይደለም እንዴ? ምን አድርጓል? ሰላም ማስከበር ካቃታቸው በኢትዮጵያ ሕግ መሠረት ”አልቻልንም፤ የፌዴራል መንግሥት ጣልቃ ይግባልን” ይባላል እኮ! መቼም ”እኔ ለዚህ ኃላፊነት ብቁ ሆኜ አልተገኘሁም፤ የተሻለ ብስለትና ልምድ ያለው ሰው ይተካኝ” የሚሉ ኃላፊዎችን በሕይወት እያለን እንደማናይ ዕሙን ነው።

ሰው ባለቀ ቁጥር ይቺን ሻማ ብልጭ ማድረግ ምን ፋይዳ አለው? ይሰለቻል። የክልሉ መንግሥት ለዚህ ዞን ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ሕዝቡን ይጠብቅ። በጊዜ መፍትሔ ካልተሰጠው የዚህ ዳፋ የማይተርፈው ሰው የለም።

እንደ አንድ ተርታ ዜጋ በደረሰው ጉዳት ሐዘኔን ለመግለጽ እወዳለሁ።

ይህ ፁሑፍ የተዘጋጀዉ በሐዉለት አሕመድ ነዉ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...