ደቡብ ሱዳን ግብፅ እና ሱዳን የዓባይ ውኃ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነትን እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቀረበች

Date:

የደቡብ ሱዳን መንግሥት ግብፅ እና ሱዳን የዓባይ ተፋሰስ አገራት የትብብር ማዕቀፍ ስምምነትን እንዲፈርሙና ፍትሐዊ የውኃ አጠቃቀም ሥርዓት እንዲሰፍን ጥሪ አቀረበ።

ጥሪው የቀረበው ትላንት እሁድ በጁባ በተከበረው የ”ዓባይ ቀን” በዓል ላይ ሲሆን፣ የደቡብ ሱዳን የውኃ ሀብትና መስኖ ሚኒስትር ጄምስ ማዊች ማኩዋች ግብፅ፣ ሱዳን፣ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ኬንያ ስምምነቱን በመቀላቀል ቀጣይነት ያለው የውኃ አስተዳደር እንዲሰፍን በጋራ እንዲሠሩ አሳስበዋል።

እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በጥቅምት 13 ቀን 2024 በይፋ ሥራ ላይ የዋለው ይህ የማዕቀፍ ስምምነት፣ እስካሁን በኢትዮጵያ፣ ሩዋንዳ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኡጋንዳ፣ ታንዛኒያ እና ቡሩንዲ መጽደቁ ይታወሳል።

ስምምነቱ የዓባይ ተፋሰስ አገራት በግዛታቸው ውስጥ ያለውን የውኃ ሀብት “በፍትሐዊና ምክንያታዊ በሆነ መንገድ” የመጠቀም መብት እንዳላቸው ይደነግጋል። ሆኖም ግብፅና ሱዳን “ስምምነቱ ከቅኝ ግዛት ዘመን ስምምነቶች ያገኘነውን ታሪካዊ መብት ይጋፋል” በሚል እስካሁን ለመፈረም ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቆይተዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...